የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘፍጥረት 15:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ያን ጊዜም የአ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ አብ​ራም እን​ዲህ ሲል መጣ፤ “እርሱ አይ​ወ​ር​ስ​ህም፤ ነገር ግን ከአ​ብ​ራ​ክህ የሚ​ወ​ጣው እርሱ ይወ​ር​ስ​ሃል።”

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል መጣለት፤ “ይህ ሰው ወራሽህ አይሆንም፤ ነገር ግን ከአብራክህ የሚከፈል ልጅ ወራሽህ ይሆናል።”

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እነሆም፥ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል መጣለት፦ ይህ አይወርስህም፥ ነገር ግን ከጉልበትህ የሚወጣው ይወርስሃል።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚህ በኋላ የእግዚአብሔር ቃል “ይህ ኤሊዔዘር የተባለው አገልጋይ የአንተን ሀብት አይወርስም፤ ከአንተ የሚወለደው ልጅ ወራሽህ ይሆናል” ብሎ ሲነግረው ሰማ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እነሆም፥ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል መጣለት፥ ይህ አይወርስህም፤ ነገር ግን ከጉልበትህ የሚወጣው ይወርስሃል።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘፍጥረት 15:4
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከዚ​ህም ነገር በኋላ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በራ​እይ ወደ አብ​ራም መጣ፤ እን​ዲህ ሲል፥ “አብ​ራም ሆይ፥ አት​ፍራ፤ እኔ ጋሻ እሆ​ን​ሃ​ለሁ፤ ዋጋ​ህም በእኔ ዘንድ እጅግ ብዙ ነው።”


እባ​ር​ካ​ታ​ለ​ሁና፥ ከአ​ን​ተም ልጆ​ችን እሰ​ጣ​ታ​ለ​ሁና፤ አሕ​ዛ​ብና የአ​ሕ​ዛብ ነገ​ሥ​ታት ከእ​ር​ስዋ ይወ​ጣሉ።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አብ​ር​ሃ​ምን አለው፥ “ስለ​ዚች አገ​ል​ጋ​ይ​ህና ስለ ሕፃኑ አት​ዘን፤ ሣራም የም​ት​ነ​ግ​ር​ህን ቃል ሁሉ ስማ፤ በይ​ስ​ሐቅ ዘር ይጠ​ራ​ል​ሃ​ልና።


ዳዊ​ትም አቢ​ሳ​ንና አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን ሁሉ፥ “እነሆ፥ ከወ​ገቤ የወ​ጣው ልጄ ነፍ​ሴን ይሻል፤ ይል​ቁ​ንስ ይህ የኢ​ያ​ሚን ልጅ እን​ዴት ነዋ? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አዝ​ዞ​ታ​ልና ተዉት፥ ይር​ገ​መኝ።


ዕድ​ሜ​ህም በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ፤ ከአ​ባ​ቶ​ች​ህም ጋር ባን​ቀ​ላ​ፋህ ጊዜ፥ ከወ​ገ​ብህ የሚ​ወ​ጣ​ውን ዘር​ህን ከአ​ንተ በኋላ አስ​ነ​ሣ​ለሁ፤ መን​ግ​ሥ​ቱ​ንም አዘ​ጋ​ጃ​ለሁ ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አ​ኩን ላከ፤ እር​ሱም ጽኑ​ዓን ኀያ​ላ​ኑ​ንና መሳ​ፍ​ን​ቱን አለ​ቆ​ቹ​ንም ከአ​ሦር ንጉሥ ሰፈር አጠፋ። የአ​ሦ​ርም ንጉሥ አፍሮ ወደ ሀገሩ ተመ​ለሰ። ወደ አም​ላ​ኩም ቤት በገባ ጊዜ ከወ​ገቡ የወ​ጡት ልጆቹ በዚያ በሰ​ይፍ ገደ​ሉት።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ እኛስ እንደ ይስ​ሐቅ የተ​ስፋ ልጆች ነን።


እርሱን እልከዋለሁ፤ አንተም ልቤ እንደሚሆን ተቀበለው።