ዘፍጥረት 15:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 እነሆም፥ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል መጣለት፦ ይህ አይወርስህም፥ ነገር ግን ከጉልበትህ የሚወጣው ይወርስሃል። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም4 በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል መጣለት፤ “ይህ ሰው ወራሽህ አይሆንም፤ ነገር ግን ከአብራክህ የሚከፈል ልጅ ወራሽህ ይሆናል።” ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 ከዚህ በኋላ የእግዚአብሔር ቃል “ይህ ኤሊዔዘር የተባለው አገልጋይ የአንተን ሀብት አይወርስም፤ ከአንተ የሚወለደው ልጅ ወራሽህ ይሆናል” ብሎ ሲነግረው ሰማ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 ያን ጊዜም የአግዚአብሔር ቃል ወደ አብራም እንዲህ ሲል መጣ፤ “እርሱ አይወርስህም፤ ነገር ግን ከአብራክህ የሚወጣው እርሱ ይወርስሃል።” ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 እነሆም፥ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል መጣለት፥ ይህ አይወርስህም፤ ነገር ግን ከጉልበትህ የሚወጣው ይወርስሃል። ምዕራፉን ተመልከት |