ትዕቢተኛውንም ከሳተ በኋላ በንስሓ ወደ እርሱ በተመለሰ ጊዜ ስለ ፍርሀትህና ስለ ድንጋጤህ ኀጢአትህን ይቅር እልሃለሁ አለው፤ የአባትን ኀጢአት በልጆች ላይ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ የማመጣ፥ ለሚወድዱኝ፥ ሕጌንም ለሚጠብቁ ግን ለእነርሱ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ምሕረትን የማደርግ ፈጣሪህ እግዚአብሔር እኔ ነኝና።