ያንጊዜም ከጕድጓዱ ወጣ፤ “እኔ እግዚአብሔርን አሳዝኜዋለሁና የወደድኸውን አድርገኝ እንጂ ከአንተ እንዳልለይ እግዚአብሔር እንዲህና እንዲህ ያድርገኝ ብሎ ለነቢዩ ሰገደ፤ ለእኛ ሕግ የለንምና እንደ አባቶች በትእዛዙ አልሄድሁም፤ አባቶቻችንም እንዳስተማሩን ጣዖት እንደምናመልክ አንተ ታውቃለህ።