1 ሳሙኤል 5:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህም የዳጎን ካህናት፥ ወደ ዳጎን ቤት የሚገቡትም ሁሉ በአዛጦን ያለውን የዳጎንን መድረክ እስከ ዛሬ ድረስ አይረግጡም፤ ይራመዱት ነበር እንጂ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዳጎን ካህናትም ሆኑ ሌሎች በአሽዶድ ወዳለው የዳጎን ቤተ ጣዖት የሚገቡ ሁሉ እስከ ዛሬ ድረስ እግራቸው ደጃፉን እንዳይረግጥ ተራምደው የሚያልፉት በዚሁ ምክንያት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዳጎን ካህናትም ሆኑ ሌሎች በአሽዶድ ወዳለው የዳጎን ቤት የሚገቡ ሁሉ እስከ ዛሬ ድረስ እግራቸው ደጃፉን እንዳይረግጥ ተራምደው የሚያልፉት በዚሁ ምክንያት ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዛሬም እንኳ ቢሆን የዳጎን ካህናትና በአሽዶድ እርሱን የሚያመልኩት ሁሉ ያን የመግቢያ መድረክ በእግራቸው ሳይረግጡ ተራምደው የሚሄዱበት ምክንያት ይኸው ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህም የዳጎን ካህናት ወደ ዳጎንም ቤት የሚገቡት ሁሉ በአዛጦን ያለውን የዳጎንን መድረክ እስከ ዛሬ ድረስ አይረግጡም። |
የእግዚአብሔርም ሠራዊት አለቃ ኢያሱን፥ “አንተ የቆምህበት ስፍራ የተቀደሰ ነውና ጫማህን ከእግርህ አውልቅ” አለው። ኢያሱም እንዲሁ አደረገ።
ጌታዋም ማለዳ ተነሣ፤ የቤቱንም ደጅ ከፈተ፤ መንገዱንም ለመሄድ ወጣ፤ እነሆም፥ ዕቅብቱ ሴት በቤቱ ደጃፍ ላይ ወድቃ፥ እጆችዋም በመድረኩ ላይ ወድቀው አገኛት።