Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 5:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 በነ​ጋ​ውም ማለዱ፤ እነ​ሆም፥ ዳጎን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቃል ኪዳን ታቦት ፊት በም​ድር ላይ በግ​ን​ባሩ ወድቆ ነበር፤ የዳ​ጎ​ንም ራስ፥ ሁለቱ እጆ​ቹም ተቈ​ር​ጠው እየ​ራ​ሳ​ቸው በመ​ድ​ረኩ ላይ ወድ​ቀው ነበር፤ ሁለቱ መሀል እጆ​ቹም በወ​ለሉ ላይ ወድ​ቀው ነበር። የዳ​ጎ​ንም ደረት ብቻ​ውን ቀርቶ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 በሚቀጥለው ቀን ጧት ተነሥተው ሲመለከቱ፣ ዳጎን በእግዚአብሔር ታቦት ፊት፣ መሬት ላይ በግንባሩ ተደፍቶ ነበር፤ ራሱና እጆቹ ተሰባብረው በደጃፉ ላይ የወደቁ ሲሆን፣ የቀረው ሌላው አካሉ ብቻ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ነገር ግን በሚቀጥለው ቀን ጠዋት ተነሥተው ሲመለከቱ፥ ዳጎን በጌታ ታቦት ፊት፥ መሬት ላይ በግንባሩ ተደፍቶ ነበር፤ ራሱና እጆቹ ተሰባብረው በደጃፉ ላይ የወደቁ ሲሆኑ፥ የቀረው ሌላው አካሉ ብቻ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 በተከታዩም ቀን ማለዳ ተነሥተው ሲመለከቱ የምስሉ ሐውልት በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት እንደገና ወድቆ አዩት፤ በዚህ ጊዜ ራሱና ሁለት እጆቹ ተሰባብረው በመግቢያው መድረክ ላይ ወድቀው ሌላው አካሉ ብቻ ቀርቶ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 በነጋውም ማለዱ፥ እነሆም፥ ዳጎን በእግዚአብሔር ታቦት ፊት በምድር ላይ በግምባሩ ወድቆ ነበር፥ የዳጎንም ራስ እጆቹም ተቆርጠው በመድረኩ ላይ ወድቀው ነበር፥ የዳጎንም ደረት ብቻውን ቀርቶ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 5:4
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የተቀረጹትም ምስሎችዋ ይደቅቃሉ፥ በግልሙትና ያገኘችው ዋጋ ሁሉ በእሳት ይቃጠላል፥ ጣዖታትዋንም ሁሉ አጠፋለሁ፥ በግልሙትና ዋጋ ሰበሰባቻቸው፥ ወደ ግልሙትናም ዋጋ ይመለሳሉና።


“ለአ​ሕ​ዛብ ተና​ገሩ፤ አው​ሩም፤ ዓላ​ማ​ው​ንም አንሡ፥ አት​ደ​ብቁ፦ ባቢ​ሎን ተያ​ዘች፤ ቤል አፈረ፤ ሜሮ​ዳክ ፈራች፤ ምስ​ሎ​ች​ዋም አፈሩ፤ ጣዖ​ታ​ቷም ደነ​ገጡ፤ በሉ።


እና​ን​ተም፦ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን ያል​ፈ​ጠሩ እነ​ዚህ አማ​ል​ክት ከም​ድር ላይ፥ ከሰ​ማ​ይም በታች ፈጽ​መው ይጥፉ ትሉ​አ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ።


ስለ​ዚ​ህም የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዶ​ችና የፀ​ሐይ ምስ​ሎች ዳግ​መኛ እን​ዳ​ይ​ነሡ የመ​ሠ​ዊ​ያ​ውን ድን​ጋይ ሁሉ እንደ ደቀቀ እንደ ኖራ ድን​ጋይ ባደ​ረገ ጊዜ ፥ እን​ዲሁ የያ​ዕ​ቆብ በደል ይሰ​ረ​ያል፤ ይህም ኀጢ​አ​ትን የማ​ስ​ወ​ገድ ፍሬ ሁሉ ነው።


እጁ ከእ​ና​ን​ተና ከአ​ማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ችሁ፥ ከም​ድ​ራ​ች​ሁም ይቀ​ልል ዘንድ፥ የእ​ባ​ጫ​ች​ሁን ምሳሌ፥ ምድ​ራ​ች​ሁ​ንም የሚ​ያ​ጠ​ፉ​ትን የአ​ይ​ጦ​ችን ምሳሌ አድ​ር​ጋ​ችሁ ለእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ክብ​ርን ስጡ።


ጠራ​ቢው የማ​ይ​ነ​ቅ​ዘ​ውን እን​ጨት ይመ​ር​ጣል፤ ምስ​ሉም እን​ዳ​ይ​ና​ወጥ ያቆ​መው ዘንድ ብልህ ሠራ​ተ​ኛን ይፈ​ል​ጋል።


ሰው ሁሉ ዕው​ቀት አጥቶ ሰን​ፎ​አል፤ አን​ጥ​ረ​ኛም ሁሉ ከቀ​ረ​ጸው ምስል የተ​ነሣ አፍ​ሮ​አል፤ ቀልጦ የተ​ሠራ ምስሉ ውሸት ነውና፥ እስ​ት​ን​ፋ​ስም የለ​ው​ምና።


አገ​ጣ​ጥ​መው የሚ​ሠ​ሩት ሥራ ከንቱ ነው፤ በተ​ጐ​በኙ ጊዜም ይጠ​ፋሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች