Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 5:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ዛሬም እንኳ ቢሆን የዳጎን ካህናትና በአሽዶድ እርሱን የሚያመልኩት ሁሉ ያን የመግቢያ መድረክ በእግራቸው ሳይረግጡ ተራምደው የሚሄዱበት ምክንያት ይኸው ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 የዳጎን ካህናትም ሆኑ ሌሎች በአሽዶድ ወዳለው የዳጎን ቤተ ጣዖት የሚገቡ ሁሉ እስከ ዛሬ ድረስ እግራቸው ደጃፉን እንዳይረግጥ ተራምደው የሚያልፉት በዚሁ ምክንያት ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 የዳጎን ካህናትም ሆኑ ሌሎች በአሽዶድ ወዳለው የዳጎን ቤት የሚገቡ ሁሉ እስከ ዛሬ ድረስ እግራቸው ደጃፉን እንዳይረግጥ ተራምደው የሚያልፉት በዚሁ ምክንያት ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ስለ​ዚ​ህም የዳ​ጎን ካህ​ናት፥ ወደ ዳጎን ቤት የሚ​ገ​ቡ​ትም ሁሉ በአ​ዛ​ጦን ያለ​ውን የዳ​ጎ​ንን መድ​ረክ እስከ ዛሬ ድረስ አይ​ረ​ግ​ጡም፤ ይራ​መ​ዱት ነበር እንጂ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ስለዚህም የዳጎን ካህናት ወደ ዳጎንም ቤት የሚገቡት ሁሉ በአዛጦን ያለውን የዳጎንን መድረክ እስከ ዛሬ ድረስ አይረግጡም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 5:5
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዚያን ቀን በአሕዛብ የአምልኮ ሥርዓት በቤተ መቅደሱ መድረክ ላይ እየዘለሉ የሚያመልኩትንና የጌታቸውን ቤት በዓመፅና በማታለል በተገኙ ዕቃዎች የሚሞሉትን ሰዎች እቀጣለሁ።”


የእግዚአብሔር ሠራዊት አዛዥም “የቆምክባት ምድር የተቀደሰች ስለ ሆነች ጫማህን አውልቅ” አለው፤ ኢያሱም እርሱ እንዳዘዘው አደረገ።


በዚያም ጧት ባልየው ጒዞውን ለመቀጠል በሩን ሲከፍት ቊባቱ እጅዋን ወደ በሩ እንደ ዘረጋች በቤቱ ፊት ለፊት ወድቃ አገኛትና፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች