ግብጻውያኑ ግን በእነርሱ ላይ የተላኩት ፍጥረታት ስለ አስጠሉዋቸው፥ እጅግ ቢራቡም የምግብ ፍላጐታቸውን ጨርሰው አጡ፤ ያንተ ሕዝቦች ግን ጥቂት ከተቸገሩ በኋላ ለየት ያለ ጣፋጭ ምግብ አገኙ።
እነዚያ ግን መብልን በተመኙ ጊዜ በእነርሱ ስለ ተላከባቸው ፍጥረት ከፍላጎታቸው ተመለሱ፥ የዘወትሩንም ልማድ ናቁ። እነዚህ ግን ምግብን በማጣት ጥቂት ወራት ከተቸገሩ በኋላ ጣዕሙ ልዩ ለሆነ ምግብ ተዘጋጁ።