ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ጥበብ 16:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 እነዚያ ግን መብልን በተመኙ ጊዜ በእነርሱ ስለ ተላከባቸው ፍጥረት ከፍላጎታቸው ተመለሱ፥ የዘወትሩንም ልማድ ናቁ። እነዚህ ግን ምግብን በማጣት ጥቂት ወራት ከተቸገሩ በኋላ ጣዕሙ ልዩ ለሆነ ምግብ ተዘጋጁ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 ግብጻውያኑ ግን በእነርሱ ላይ የተላኩት ፍጥረታት ስለ አስጠሉዋቸው፥ እጅግ ቢራቡም የምግብ ፍላጐታቸውን ጨርሰው አጡ፤ ያንተ ሕዝቦች ግን ጥቂት ከተቸገሩ በኋላ ለየት ያለ ጣፋጭ ምግብ አገኙ። ምዕራፉን ተመልከት |