መልአኩም “ዓሣውን እረደውና ሐሞቱን፥ ልቡንና ጉበቱን አውጣው፤ እነዚህን ያዝና የሆድ እቃውን ወዲያ ጣለው፤ ሐሞቱ፥ ልቡና ጉበቱ ለመድኃኒትነት ይጠቅማልና” አለው።
ያም ልጅ መልአኩ እንዳዘዘው አደረገ፤ ዓሣውንም ጠብሰው በሉ፤ ሁለቱም ገሥግሠው ሄደው፥ ወደ በጣኔስ ደረሱ።