በዚያ ሰዓት ወደ መስኮቱ እጆችዋን ዘርግታ እንዲህ ስትል ጸለየች፦ “መሐሪ አምላክ ሆይ፥ የተባረክ ነህ፥ ስምህ ለዘለዓለም ብሩክ ይሁን፥ የሠራሃቸው ነገሮች በሙሉ ለዘለዓለም ይባርኩህ።
በመስኮቱም በኩል ጸለየች፤ እንዲህም አለች፥ “አቤቱ አንተ ፈጣሪዬ ቡሩክ ነህ፤ ቅዱስና ክቡር ስምህም ለዘለዓለም ይመስገን፤ ሥራህም ሁሉ ለዘለዓለሙ ክቡር ነው።