አንተና ሣራ በጸሎት ላይ በነበራችሁ ጊዜ ጸሎታችሁን በጌታ ክብር ፊት ያቀረብሁና ያነበብሁ እኔ ነኝ፥ አንተም የሞቱትን ሰዎች ሬሳ ስትቀብር እንዲሁ።
እነሆ፥ አንተና ምራትህ ሣራ በጸለያችሁ ጊዜ የልመናችሁን መታሰቢያ እኔ በቅዱሱ ፊት አቀረብሁ፤ አንተም ሬሳ በቀበርህ ጊዜ ያንጊዜ እኔ ካንተ ጋራ ነበርሁ።