በደስታ ሸኛቸው፤ ጦብያን ሲሰናበተው እንዲህ አለው “ልጄ ደኀና ሁን፥ መልካም ጉዞ፥ የሰማዩ ጌታ አንተንና ሚስትህ ሣራን ሞገስ ይሁናችሁ፥ ከመሞቴ በፊት ልጆቻችሁን ለማየት ያብቃኝ።”
ራጉኤልም ተነሥቶ ሚስቱ ሣራንና፥ የገንዘቡን እኩሌታ፥ አገልጋዮችን፥ ከብቶችንም፥ ብሩንም ሰጠው።