ጠላቶቻቸውን ፈጥኜ ባዋረድኋቸው ነበር፥ በሚያስጨንቋቸውም ላይ እጄን በጣልሁ ነበር፥
እግዚአብሔርን የሚጠሉ በፊቱ ይርዳሉ፤ ቅጣታቸውም እስከ ዘላለም የሚዘልቅ ነው።
እኔን የሚጠሉ ሁሉ በፍርሃት በእግሬ ሥር ይደፋሉ፤ ቅጣታቸውም ለዘለዓለም ይጸናል።
አንተ ግን ያው አንተ ነህ፥ ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም።
ኃይልህንና ክብርህን አይ ዘንድ እንዲሁ በመቅደስ ውስጥ ተመለከትሁህ።
አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውም፤ እኔ ጌታ አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፥
ሌላ እንዲቀመጥበት አይሠሩም፥ ሌላም እንዲበላው አይተከሉም፤ የሕዝቤ ዕድሜ እንደ ዛፍ ዕድሜ ይሆናልና፥ እኔም የመረጥኋቸው በእጃቸው ሥራ ረጅም ዘመን ደስ ይላቸዋል።
ነገር ግን ይሁዳ ለዘለዓለም፥ ኢየሩሳሌምም ለልጅ ልጅ መኖሪያ ይሆናል።
“በሥርዓቶቼ ብትመላለሱ፥ ትእዛዛቴንም ብትጠብቁ ብታደርጉአቸውም፥
ጠላቶቻችሁንም ታሳድዳላችሁ፥ በእናንተም ፊት በሰይፍ ይወድቃሉ።
ሐሜተኞች፥ አምላክን የሚጠሉ፥ የሚዳፈሩ፥ ትዕቢተኞች፥ ትምክህተኞች፥ ክፋትን የሚያውጠነጥኑ፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥
ስለ ሥጋ ማሰብ የእግዚአብሔር ጠላት መሆን ነው፤ ለእግዚአብሔር ሕግ አይገዛምና፥ መገዛትም አይችልም፥
የሚጠሉትን በማጥፋት በፊታቸው ብድራት ይመልስባቸዋል፥ ለሚጠላው አይዘገይም፥ በፊቱ ብድራት ይመልስበታል።