መዝሙር 69:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጥልቅ ረግረግ ጠለቅሁ መቆሚያም የለኝም። ወደ ጥልቅ ባሕር ገባሁ ማዕበልም አሰጠመኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጩኸት ደከምሁ፤ ጕረሮዬም ደረቀ፤ አምላኬን በመጠባበቅ፣ ዐይኖቼ ፈዘዙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከመጮኼ ብዛት የተነሣ ደከምኩ፤ ጒሮሮዬም ቈሰለ፤ አምላኬን በመጠባበቅ ዐይኖቼ ፈዘዙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እሰይ! እሰይ! የሚሉኝ አፍረው ወዲያው ወደ ኋላቸው ይመለሱ። |
ካፍ። ሕፃኑና ጡት የሚጠባው በከተማይቱ ጐዳና ላይ ሲዝሉ፥ ዓይኔ በእንባ ደከመች፥ አንጀቴም ታወከ፥ ስለ ወገኔ ሴት ልጅ ቅጥቃጤ ጉበቴ በምድር ላይ ተዘረገፈ።
ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ ለሌላ ሕዝብ ይሰጣሉ፤ ነገር ግን ምንም ለማድረግ አትችልም፤ ከዛሬ ነገ ይመጣሉ በማለትም ዐይኖችህ ሁልጊዜ እነርሱን በመጠባበቅ ይደክማሉ።
እርሱም ሥጋ ለብሶ በምድር በሚመላለስ ጊዜ፥ ከሞት ሊያድነው ወደሚችል፥ ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፤ ስለ ጻድቅ ፍርሃቱም ጸሎቱ ተሰማለት፤