Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 38:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 እንደ ጨረባና እንደ ሽመላ ተንጫጫሁ፥ እንደ ርግብም አጉረመረምሁ፤ ዐይኖቼ ወደ ላይ በማየት ደከሙ። ጌታ ሆይ፥ ተጨንቄአለሁና መከታ ሁነኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 እንደ ጨረባ፣ እንደ ሽመላም ተንጫጫሁ፤ እንደ ርግብ አልጐመጐምሁ፤ ዐይኖቼ ወደ ሰማይ በመመልከት ደከሙ፤ ጌታ ሆይ፤ ተጨንቄአለሁና ታደገኝ!”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 እንደ ሽመላ እጮኽ ነበር፤ እንደ ርግብ የሐዘን ድምፅ አሰማ ነበር፤ ወደ ሰማይም አሻቅቤ ከመመልከቴ የተነሣ፥ ዐይኖቼ በጣም ደክመው ነበር። ጌታ ሆይ! እባክህን ከዚህ ሁሉ መከራ አድነኝ!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 እንደ ሸመላ እን​ዲሁ ጮህሁ፤ እንደ ርግ​ብም አጕ​ረ​መ​ረ​ምሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 እንደ ጨረባና እንደ ሽመላ ተንጫጫሁ፥ እንደ ርግብም አጕረመረምሁ፥ ዓይኖቼ ወደ ላይ ከማየት ደከሙ። ጌታ ሆይ፥ ተጨንቄአለሁና መከታ ሁነኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 38:14
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሁላችን እንደ ድቦች እንጮኻለን፤ እንደ ርግብ በመቃተት እንጮኻለን፤ ፍትህን በተስፋ እንጠባበቅ ነበር እርሱ ግን የለም፤ መዳንም ከእኛ ዘንድ ርቆአል።


በጥልቅ ረግረግ ጠለቅሁ መቆሚያም የለኝም። ወደ ጥልቅ ባሕር ገባሁ ማዕበልም አሰጠመኝ።


የወንዞቹ በሮች ተከፈቱ፥ ቤተ መንግሥቱም ቀለጠ።


ከእነርሱም የሚሸሹ ያመልጣሉ፥ እንደ ሸለቆ እርግቦች በተራራ ላይ ይሆናሉ፥ ሁሉም በኃጢአታቸው ላይ ያቃስታሉ።


ለቀበሮ ወንድም፥ ለሰጐንም ባልንጀራ ሆንሁ።


ፌ። ዓይናችን ወደ ከንቱ ረዳታችን ገና ሲመለከት ጠፍቶአል፥ በመቆየታችን ማዳን የማይቻለውን ሕዝብ ጠብቀናል።


አቤቱ፥ ፈጥነህ ስማኝ፥ መንፈሴ ዛለ፥ ፊትህን ከኔ አትሰውር፥ ወደ ጉድጓድም እንደሚወርዱ እንዳልሆን።


መቼ ታጽናናኛለህ እያልሁ ዐይኖቼ ስለ ቃልህ ፈዘዙ።


“እባክህን፥ አንተ ዋስ ሁነኝ፥ ለእኔ ተያዥ የሚሆነኝ ማን ነው?


በዚህ መሐላ ምክንያት ኢየሱስ ለተሻለው ቃል ኪዳን ዋስ ሆኖአል።


አቤቱ፥ ጸሎቴን አድምጥ፥ ልመናዬንም ቸል አትበል።


ቆሟል፥ ተገለጠች፥ ተማረከች፥ ሴቶች አገልጋዮቿም እንደ ርግብ እየጮኹና ደረታቸውን እየመቱ አለቀሱ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች