ልቅሶዬን ወደ እልልታ ለወጥህልኝ፥ ማቄን ቀድደህ ደስታንም አስታጠቅኸኝ።
እንግዲህ ነፍሴ ታመስግንህ፤ ዝምም አትበል፤ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ ለዘላለም አመሰግንሃለሁ።
ስለዚህ ዝም አልልም፤ ለአንተ የምስጋና መዝሙር አቀርባለሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ! አንተ አምላኬ ነህ፤ ስለዚህ ለዘለዓለም አመሰግንሃለሁ።
እንደ ሞተ ሰው ከልብ ረሱኝ፥ እንደ ጠፋ ዕቃም ሆንሁ።
በምክራቸው፥ ነፍሴ፥ አትግባ፥ ከጉባኤአቸውም ጋር፥ ክብሬ፥ አትተባበር፥ በቁጣቸው ሰውን ገድለዋልና፥ በገዛ ፈቃዳቸውም በሬን አስነክሰዋልና።
እኔ ግን በቸርነትህ ታመንሁ፥ ልቤም በማዳንህ ደስ ይለዋል። ለረዳኝን ጌታ እዘምራለሁ፥ መልካምን አድርጎልኛልና።
በየቀኑ ሁሉ እባርክሃለሁ፥ ስምህንም ለዘለዓለም ዓለምም አመሰግናለሁ።
ስለዚህ ልቤን ደስ አለው ነፍሴም ሐሴት አደረገች፥ ሥጋዬም ደግሞ በተስፋ ታድራለች፥
አንተ ግን ከጠላቶቻችን አዳንኸን፥ የሚጠሉንንም አሳፈርሃቸው።
ልቤ ጽኑ ነው፥ አቤቱ፥ ልቤ ጽኑ ነው፥ እቀኛለሁ፥ እዘምራለሁ።
እኔ ግን ሁልጊዜ ተስፋ አደርጋለሁ፥ በምስጋናህም ሁሉ ላይ እጨምራለሁ።
ዝማሬን ባቀርብሁልህ ጊዜ ከንፈሮቼ ደስ ይላቸዋል፥ አንተ ያዳንሃትም ነፍሴ እንዲሁ።
ጌታ ለክብሩ የተከላቸው ጽድቃዊ የባሉጥ ዛፎች እንዲባሉ ለጽዮን አልቃሾች በአመድ ፋንታ አክሊልን እንዳደርግላቸው፥ በልቅሶም ፋንታ የደስታን ዘይት፥ በኀዘን መንፈስ ፋንታ የምስጋናን መጐናጸፊያ እንድሰጣቸው ልኮኛል።
ሲመልስም “እነዚህ እንኳ ዝም ቢሉ ድንጋዮች ይጮኻሉ፤እላችኋለሁ” አላቸው።
እኛስ ያየነውንና የሰማነውን ከመናገር ዝም ማለት አንችልም፤” አሉአቸው።
“አሜን ውዳሴ፥ ክብር፥ ጥበብ፥ ምስጋና ገናናነት፥ ክብር ኃይልና ብርታት ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ድረስ ለአምላካችን ይሁን! አሜን።” አሉ።