ምሳሌ 18:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰነፍ የጥበብን ነገር አይወድድም፥ በልቡ ያለውን ሁሉ መግለጥ ብቻ ይወድዳል እንጂ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሞኝ ከማስተዋል ርካታን አያገኝም፤ የራሱን ሐሳብ በመግለጥ ግን ደስ ይለዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሞኝ የራሱን አስተያየት ብቻ መግለጥ ይፈልጋል እንጂ ዕውቀትን ከሌላ ሰው መገብየት ደስ አያሰኘውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዕውቀት ድሃ ጥበብን አይወድድም፤ ነገር ግን ስንፍና ይገዛዋል። |
እናንተም እንደዚሁ ናችሁ፤ መንፈሳዊ ስጦታዎችን ለማግኘት የምትሹ በመሆናችሁ፥ ቤተ ክርስቲያን የምትታነጽበትን ስጦታዎች ለማግኘት ይበልጥ ፈልጉ።