ዘኍል 23:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔር ያልረገመውን እንዴት እረግማለሁ? ጌታስ ያላወገዘውን እንዴት አወግዛለሁ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ያልረገመውን፣ እኔ እንዴት ረግማለሁ? እግዚአብሔር ያላወገዘውንስ፣ እንዴት አወግዛለሁ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታዲያ፥ እኔ እግዚአብሔር ያልረገመውን እንዴት እረግመዋለሁ? እግዚአብሔር ያላወገዘውንስ እንዴት አወግዛለሁ? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ያልረገመውን እንዴት እረግማለሁ? እግዚአብሔርስ ያልተጣላውን እንዴት እጣላለሁ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር ያልረገመውን እንዴት እረግማለሁ? እግዚአብሔርስ ያልተጣላውን እንዴት እጣላለሁ? |
አሁንም ከእኔ ይልቅ እጅግ ኃያል ናቸውና ልወጋቸውና ከምድሪቱ ላሳድዳቸው እችል እንደሆነ፥ ይህን ሕዝብ እባክህ፥ ና ርገምልኝ፤ አንተ የባረከው ቡሩክ የረገምኸውም ርጉም እንደሆነ አውቃለሁና።”
በያዕቆብ ላይ አስማት የለም፥ በእስራኤልም ላይ ምዋርት የለም፤ በጊዜው ስለ ያዕቆብና ስለ እስራኤል እንዲህ ይባላል፦ ‘እግዚአብሔር ምን አደረገ!’
በለዓምም ምሳሌውን ይመስል ጀመር፥ እንዲህም አለ፦ “ባላቅ ከአራም አመጣኝ፥ የሞዓብ ንጉሥ ከምሥራቅ ተራሮች፤ ‘ና፥ ያዕቆብን ርገምልኝ፤ ና፥ እስራኤልን አውግዝልኝ አለኝ።’