ነህምያ 5:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህ የሚሉ ነበሩ፦ “እኛ፥ ወንዶች ልጆቻችንና ሴቶች ልጆቻችን ብዙ ነን፤ እንድንበላና በሕይወት እንድንኖር እህልን እንውሰድ” አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንዳንዶቹ፣ “እኛም ሆነ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችን በቍጥር ብዙ ነን፤ ታዲያ ለመብላትም ሆነ በሕይወት ለመቈየት እህል ማግኘት አለብን” አሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእነርሱም አንዳንዶቹ “ብዙ ቤተሰብ ስላለን ሕይወታችንን ለማትረፍ የሚያስችለን እህል እንፈልጋለን” አሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ከወንዶችና ሴቶች ልጆቻችን ጋር ብዙዎች ነን፤ በልተንም በሕይወት እንድንኖር እህልን እንሸምት” የሚሉ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አያሌዎቹም፦ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችን ብዙዎች ናቸው፥ በልተንም በሕይወት እንድንኖር እህልን እንሸምት ይሉ ነበር። |
ይሁዳም አባቱን እስራኤልን እንዲህ አለው “ልጁን ከእኔ ጋር ስደደው፤ እኛም በቶሎ እንሂድ፤ ይህ ከሆነ፥ አንተም፥ እኛም፥ ልጆቻችንም አንሞትም፤ እንተርፋለን።
እኛ በፈትህ ስለምን እንሞታለን? ምድራችንስ ስለምን ትጠፋለች? እኛንም ምድራችንንም በእህል ግዛን፥ እኛም ለፈርዖን ባርያዎች እንሁን፥ ምድራችንም ለእርሱ ትሁን፥ እኛ እንድንድን እንዳንሞትም ምድራችንም እንዳትጠፋ ዘር ስጠን።”
የነቢያት ጉባኤ አባል የነበረ ባሏ የሞተባት አንዲት ሴት ወደ ኤልሳዕ መጥታ “ጌታዬ ሆይ! ባሌ ሞቶብኛል! እርሱም አንተ እንደምታውቀው እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ነበር፤ ነገር ግን እነሆ ለባሌ ገንዘብ አበድሮት የነበረ አንድ ሰው በባሌ ዕዳ ፈንታ ሁለት ወንዶች ልጆቼን ወስዶ ባርያ አድርጎ ሊገዛቸው ፈልጎአል” አለችው።
ብዙ ዘራችሁ፥ ጥቂትም አገባችሁ፤ በላችሁ፥ ነገር ግን አልጠገባችሁም፤ ጠጣችሁ፥ ነገር ግን አልሰከራችሁም፤ ለበሳችሁ፥ ነገር ግን አልሞቃችሁም፤ ደመወዙን የተቀበለ ሰው በቀዳዳ ከረጢት ለማስቀመጥ ደመወዙን ተቀበለ።
“ባትሰሙ፥ ለስሜም ክብር ለመስጠት በልባችሁ ባታኖሩት፥” ይላል የሠራዊት ጌታ፥ “እርግማን እልክባችኋለሁ፥ በረከታችሁንም እረግማለሁ፤ አሁንም ረግሜዋለሁ ምክንያቱም በልባችሁ አላደረጋችሁትምና።”