Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ነህምያ 5:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 “ከወ​ን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ችን ጋር ብዙ​ዎች ነን፤ በል​ተ​ንም በሕ​ይ​ወት እን​ድ​ን​ኖር እህ​ልን እን​ሸ​ምት” የሚሉ ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 አንዳንዶቹ፣ “እኛም ሆነ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችን በቍጥር ብዙ ነን፤ ታዲያ ለመብላትም ሆነ በሕይወት ለመቈየት እህል ማግኘት አለብን” አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 እንዲህ የሚሉ ነበሩ፦ “እኛ፥ ወንዶች ልጆቻችንና ሴቶች ልጆቻችን ብዙ ነን፤ እንድንበላና በሕይወት እንድንኖር እህልን እንውሰድ”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ከእነርሱም አንዳንዶቹ “ብዙ ቤተሰብ ስላለን ሕይወታችንን ለማትረፍ የሚያስችለን እህል እንፈልጋለን” አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 አያሌዎቹም፦ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችን ብዙዎች ናቸው፥ በልተንም በሕይወት እንድንኖር እህልን እንሸምት ይሉ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ነህምያ 5:2
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ለስሜ ክብር ትሰጡ ዘንድ ባትሰሙ፥ በልባችሁም ባታደርጉት፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ እርግማን እሰድዳባችኋለሁ፥ በረከታችሁንም እረግማታለሁ፣ አሁንም በልባችሁ አላደረጋችሁትምና እኔ ረግሜአታለሁ።


ይሁ​ዳም አባ​ቱን እስ​ራ​ኤ​ልን አለው፥ “እኛና አንተ ልጆ​ቻ​ች​ንም ደግሞ እን​ድ​ን​ድን፥ እን​ዳ​ን​ሞ​ትም ብላ​ቴ​ና​ውን ከእኔ ጋር ላከው፤ እኛም ተነ​ሥ​ተን እን​ሄ​ዳ​ለን።


እን​ዲ​ህም አለ፥ “እነሆ፥ እህል በግ​ብፅ እን​ዳለ ሰም​ቼ​አ​ለሁ፤ ወደ​ዚያ ውረዱ፤ እን​ድ​ን​ድ​ንና በራብ እን​ዳ​ን​ሞ​ትም ከዚያ ሸም​ቱ​ልን።”


ሀገ​ሮ​ችም ሁሉ ከዮ​ሴፍ እህል ይገዙ ዘንድ ወደ ግብፅ ወጡ፤ በም​ድር ሁሉ ራብ እጅግ ጸንቶ ነበ​ርና።


“ለወ​ን​ድ​ምህ በወ​ለድ አታ​በ​ድር፤ የብር ወይም የእ​ህል፥ ወይም የማ​ና​ቸ​ው​ንም ነገር ሁሉ ወለድ አት​ው​ሰድ።


ከነ​ቢ​ያ​ትም ልጆች የአ​ንዱ ሚስት የሆ​ነች አን​ዲት ሴት፥ “ባሌ ባሪ​ያህ ሞቶ​አል፤ ባሪ​ያ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ ሰው እንደ ነበረ አንተ ታው​ቃ​ለህ፤ ባለ ዕዳም ሁለቱ ልጆ​ቼን ባሪ​ያ​ዎች አድ​ርጎ ሊወ​ስ​ዳ​ቸው መጥ​ቶ​አል” ብላ ወደ ኤል​ሳዕ ጮኸች።


“ከራብ የተ​ነ​ሣም እህ​ልን እን​ሸ​ምት ዘንድ እር​ሻ​ች​ን​ንና ወይ​ና​ች​ንን፥ ቤታ​ች​ን​ንም አስ​ይ​ዘ​ናል” የሚሉ ነበሩ።


ብዙ ዘራችሁ፥ ጥቂትም አገባችሁ፣ በላችሁ፥ ነገር ግን አልጠገባችሁም፣ ጠጣችሁ፥ ነገር ግን አልረካችሁም፣ ለበሳችሁ፥ ነገር ግን አልሞቃችሁም፣ ደመወዙን የተቀበለ ሰው በቀዳዳ ከረጢት ያደርገው ዘንድ ደመወዙን ተቀበለ።


እን​ግ​ዲህ እኛ በፊ​ትህ እን​ዳ​ን​ሞት፥ ምድ​ራ​ች​ንም እን​ዳ​ት​ጠፋ፥ እኛ​ንም፥ ምድ​ራ​ች​ን​ንም በእ​ህል ግዛን፤ እኛም ለፈ​ር​ዖን አገ​ል​ጋ​ዮች እን​ሁን፤ ምድ​ራ​ች​ንም ለእ​ርሱ ትሁን፤ እኛ እን​ድ​ን​ድን፥ እን​ዳ​ን​ሞ​ትም፥ ምድ​ራ​ች​ንም እን​ዳ​ት​ጠፋ እን​ዘራ ዘንድ ዘር ስጠን።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች