እንዲሁም አንድ ቤተሰብ እርስ በርሱ ከተለያየ ያ ቤተሰብ ሊቆም አይችልም።
ቤትም እርስ በርሱ ከተከፋፈለ ሊቆም አይችልም።
እንዲሁም አንድ ቤተሰብ እርስ በርሱ ከተለያየ ጸንቶ መኖር አይችልም፤
ቤትም እርስ በርሱ ከተለያየ ያ ቤት ሊቆም አይችልም።
ወንድሞቹም አባታቸው ከልጆቹ ሁሉ ይልቅ እንደሚወደው ባዩ ጊዜ ጠሉት፥ በሰላም ሊያናግሩትም አልቻሉም።
የዳዊት የዕርገት መዝሙር። ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ፥ እነሆ፥ እንዴት መልካም፥ እንዴት ውብ ነው።
መንግሥትም እርስ በርስዋ ከተለያየች ያች መንግሥት ልትቆም አትችልም፤
ሰይጣንም ራሱን ተቃውሞ ቢነሣና ቢለያይ መጨረሻው ይሆንበታል እንጂ ሊቆም አይችልም።
ነገር ግን እርስ በርሳችሁ የምትነካከሱና የምትበላሉ ከሆነ እርስ በርሳችሁ እንዳትጠፋፉ ተጠንቀቁ።
ቅናትና ራስ ወዳድነት ባሉበት ስፍራ በዚያ ሁከትና ክፉ ሥራ ሁሉ ይኖራሉ።