እስራኤላውያን ይህን የፍርድ ውሳኔ በሰሙ ጊዜ ሰሎሞን የሕዝብ ጉዳዮችን በትክክለኛ ፍርድ የሚወስንበትን ጥበብ እግዚአብሔር የሰጠው መሆኑን ስለ ተገነዘቡ ታላቅ አክብሮት ሰጡት።
ኢያሱ 4:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም ቀን ጌታ ኢያሱን በእስራኤል ሁሉ ፊት ከፍ አደረገው፤ ሙሴንም ይፈሩት እንደ ነበር እንዲሁ ኢያሱን በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ፈሩት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያች ዕለት እግዚአብሔር ኢያሱን በእስራኤል ሁሉ ፊት ከፍ ከፍ አደረገው፤ ሕዝቡ ሙሴን እንዳከበሩት ሁሉ፣ ኢያሱንም በሕይወት ዘመኑ ሁሉ አከበሩት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ቀን እግዚአብሔር ኢያሱን በእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ፊት ከፍ ከፍ አደረገው፤ ሙሴን ያከብሩት እንደ ነበር ኢያሱንም በሕይወቱ ዘመን ሁሉ አከበሩት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ቀን እግዚአብሔር ኢያሱን በእስራኤል ልጆች ሁሉ ፊት ከፍ አደረገው፤ ሙሴንም እንደ ፈሩ በዕድሜው ሁሉ ፈሩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ቀን እግዚአብሔር ኢያሱን በእስራኤል ሁሉ ፊት ከፍ አደረገው፥ ሙሴንም እንደ ፈሩ በዕድሜው ሁሉ ፈሩት። |
እስራኤላውያን ይህን የፍርድ ውሳኔ በሰሙ ጊዜ ሰሎሞን የሕዝብ ጉዳዮችን በትክክለኛ ፍርድ የሚወስንበትን ጥበብ እግዚአብሔር የሰጠው መሆኑን ስለ ተገነዘቡ ታላቅ አክብሮት ሰጡት።
ከኢያሪኮ የመጡት ነቢያት እርሱን ባዩት ጊዜ “በኤልያስ ላይ ዐድሮ የነበረው የመንፈስ ኃይል በኤልሳዕ ላይ አርፏል!” አሉ፤ ወደ እርሱም በመቅረብ ጐንበስ ብለው እጅ ነሡት
ለመልካም ነገር ለአንተ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነውና። ክፉ ብታደርግ ግን ፍራ፤ በከንቱ ሰይፍ አይታጠቅምና፤ ቁጣውን ለማሳየት ክፉ አድራጊውን የሚበቀል የእግዚአብሔር አገልጋይ ነውና።
ጌታም ኢያሱን እንዲህ አለው፦ “ከሙሴ ጋር እንደ ነበርሁ እንዲሁ ከአንተ ጋር መሆኔን እንዲያውቁ በዚህ ቀን አንተን በእስራኤል ሁሉ ዘንድ ከፍ ከፍ ማድረግ እጀምራለሁ።