Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ዜና መዋዕል 30:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ደግሞም አንድ ልብ እንዲሰጣቸው፥ በጌታም ቃል የሆነውን የንጉሡንና የሹማምንቱን ትእዛዝ እንዲያደርጉ የጌታ እጅ በይሁዳ ላይ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 እንዲሁም ንጉሡና ሹማምቱ በእግዚአብሔር ቃል መሠረት ያዘዙትን እንዲፈጽሙ አንድ ልብ ይሰጣቸው ዘንድ የእግዚአብሔር እጅ በይሁዳ ላይ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ደግሞም አንድ ልብ ይሰጣቸው ዘንድ፥ በእግዚአብሔር ቃል የሆነውን የንጉሡንና የባለሥልጣኖቹን ትእዛዝ ያደርጉ ዘንድ እግዚአብሔር የይሁዳን ሕዝብ ልብ አነሣሣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ደግ​ሞም አንድ ልብ ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል የሆ​ነ​ውን የን​ጉ​ሡ​ንና የአ​ለ​ቆ​ቹን ትእ​ዛዝ ያደ​ርጉ ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በእ​ነ​ርሱ ላይ ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ደግሞም አንድ ልብ ይሰጣቸው ዘንድ፥ በእግዚአብሔርም ቃል የሆነውን የንጉሡንና የአለቆቹን ትእዛዝ ያደርጉ ዘንድ፥ የእግዚአብሔር እጅ በይሁዳ ላይ ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ዜና መዋዕል 30:12
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ወንድሞቻቸውንም ሰብስበው ተቀደሱ፤ የጌታንም ቃላት መሠረት አድርጎ ንጉሡ እንዳዘዘው የጌታን ቤት ለማንጻት ገቡ።


ይህንም ትእዛዝ ጌታ በነቢያቱ እጅ አዝዞአልና እንደ ዳዊትና እንደ ንጉሡ ባለ ራእይ እንደ ጋድ፥ እንደ ነቢዩም እንደ ናታን ትእዛዝ፥ ጸናጽልና በገና መሰንቆም አስይዞ ሌዋውያንን በጌታ ቤት አቆመ።


ሕዝቅያስና ሕዝቡም ሁሉ ጌታ ለሕዝቡ ስላዘጋጀላቸው ነገር ደስ አላቸው። ይህም ነገር በድንገት ተደረገ።


እነርሱም ንጉሡ ስለ ነገሩ ሁሉና ስለ መዝገቡ ካህናቱንና ሌዋውያኑን ያዘዘውን ነገር ሁሉ አልተላለፉም።


በኢየሩሳሌም ያለውን የጌታን ቤት እንዲያሳምር እንደዚህ ያለውን ነገር በንጉሡ ልብ ያኖረ፥ የአባቶቻችን አምላክ ጌታ ይባረክ።


ግርማዊ ክብር ከልደትህ ጊዜ አንሥቶ፥ የተቀደሰ ሞገስም ከማኅጸን፥ የወጣትነትም ጠል የአንተ ነው።


እኔም ጌታ እንደሆንሁ የሚያውቅ ልብ እሰጣቸዋለሁ፤ በፍጹምም ልባቸው ወደ እኔ ይመለሳሉና፥ ሕዝብ ይሆኑኛል እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ።


እኔን ለዘለዓለም በመፍራት ለእነርሱም ከእነርሱም በኋላ ለልጆቻቸው መልካም እንዲሆንላቸው አንድ ልብና አንድ መንገድ እሰጣቸዋለሁ።


አዲስ ልብ እሰጣችኋለሁ፥ አዲስ መንፈስ በውስጣችሁ አኖራለሁ፤ የድንጋያማ ልብ ከሥጋችሁ አወጣለሁ፥ የሥጋ ልብ እሰጣችኋለሁ።


ጴጥሮስና ዮሐንስ ግን መልሰው “እግዚአብሔርን ከመስማት ይልቅ እናንተን እንሰማ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት የሚገባ እንደሆነ ቁረጡ፤


ብቃታችን ከእግዚአብሔር ነው እንጂ፥ በገዛ እጃችን የሚሆን አንዳችን ነገር ልናስብ እኛ የበቃን አይደለንም፤


እኔ ያዘዝኋችሁን የጌታ አምላካችሁን ትእዛዝ ትጠብቃላችሁ እንጂ ባዘዝኋችሁ ቃል ላይ አትጨምሩም፥ ከእርሱም አታጎድሉም።


በጎ ፈቃዱን እንድትፈልጉና እንድታደርጉ ሁለቱንም በእናንተ ውስጥ የሚሠራ እግዚአብሔር ነውና።


በጌታ በኢየሱስ ስም ምን ዓይነት መመሪያዎች እንደ ሰጠናችሁ ታውቃላችሁና።


በዘላለም ኪዳን ደም የበጎች ታላቅ እረኛ የሆነውን ጌታችን ኢየሱስን ከሞት ያስነሣው የሰላም አምላክ፥


በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን በእናንተ እያደረገ፥ ፈቃዱን ትፈጽሙ ዘንድ በመልካም ሥራ ሁሉ ፍጹማን ያድርጋችሁ፤ ለእርሱ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች