ዳዊት ሕዝቡን ከቆጠረ በኋላ ኅሊናው ወቀሰው፤ ዳዊትም ጌታን፥ “ባደረግሁት ነገር የፈጸምኩት ታላቅ ኃጢአት ነው፤ አሁን ግን፥ ጌታ ሆይ፤ የአገልጋይህን በደል ይቅር እንድትል እለምንሃለሁ፤ የፈጸምኩት ታላቅ የሞኝነት ሥራ ነውና” አለ።
ኢዩኤል 2:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁንስ፥ ይላል ጌታ፥ በፍጹም ልባችሁ፥ በጾምም፥ በልቅሶና በዋይታ ወደ እኔ ተመለሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አሁንም ቢሆን፣ በጾም፣ በልቅሶና በሐዘን፣ በፍጹም ልባችሁ ወደ እኔ ተመለሱ” ይላል እግዚአብሔር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “አሁንም ቢሆን በጾም፥ በለቅሶና በሐዘን በፍጹም ልባችሁ ወደ እኔ ተመለሱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንስ ይላል አምላካችሁ እግዚአብሔር፥ “በፍጹም ልባችሁ በጾም፥ በልቅሶና በዋይታ ወደ እኔ ተመለሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንስ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በፍጹም ልባችሁ፥ በጾምም፥ በልቅሶና በዋይታ ወደ እኔ ተመለሱ። |
ዳዊት ሕዝቡን ከቆጠረ በኋላ ኅሊናው ወቀሰው፤ ዳዊትም ጌታን፥ “ባደረግሁት ነገር የፈጸምኩት ታላቅ ኃጢአት ነው፤ አሁን ግን፥ ጌታ ሆይ፤ የአገልጋይህን በደል ይቅር እንድትል እለምንሃለሁ፤ የፈጸምኩት ታላቅ የሞኝነት ሥራ ነውና” አለ።
እንደ ንጉሡም ትእዛዝ መልክተኞቹ እንዲህ የሚለውን የንጉሡንና የሹማምንቱን ደብዳቤ ይዘው ወደ እስራኤልና ወደ ይሁዳ ሁሉ ሄዱ እንዲህም አሉ፦ “የእስራኤል ልጆች ሆይ! ጌታ ከአሦር ነገሥታት እጅ ወዳመለጠ የእናንተ ወደ ሆኑት ትሩፋን እንዲመለስ ወደ አብርሃምና ወደ ይስሐቅ ወደ እስራኤልም አምላክ ተመለሱ።
አንተ በሰማይ ሆነህ ስማ፥ የባርያዎችህንና የሕዝብህን የእስራኤልን ኃጢአት ይቅር በል፥ የሚሄዱበትንም መልካም መንገድ አሳያቸው፤ ለሕዝብህም ርስት አድርገህ ለሰጠሃት ምድር ዝናብን ስጥ።
ጌታም ሙሴን፦ “ለእስራኤል ልጆች ‘እናንተ አንገተ ደንዳና ሕዝብ ናችሁ፥ አንድ ጊዜ ከእናንተ ጋር ብወጣ አጠፋችኋለሁ፤ አሁንም በእናንተ ላይ የማደርገውን እንዳውቅ ጌጣችሁን አውጡ’ በላቸው አለው።”
ጌታ በዚህ ሕዝብ ላይ የተናገረው ቁጣውና መዓቱ ታላቅ ነውና ምናልባት ልመናቸው በጌታ ፊት ይቀርብ ይሆናል፥ ሁሉም ከክፉ መንገዱ ይመለስ ይሆናል።”
በሕያውነቴ እምላለሁ ኃጢአተኛው ሰው ከመንገዱ ተመልሶ በሕይወት እንዲኖር እንጂ ኃጢአተኛው እንዲሞት አልፈቅድም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ የእስራኤል ቤት ሆይ ተመለሱ፥ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፤ ስለ ምንስ ትሞታላችሁ? በላቸው።
የእህሉ ቁርባንና የመጠጡ ቁርባን ከአምላካችሁ ቤት ቀርቶአልና እናንተ ካህናት፥ ማቅ ታጥቃችሁ አልቅሱ፥ እናንተም የመሠዊያ አገልጋዮች፥ ዋይ በሉ፥ እናንተ የአምላኬ አገልጋዮች፥ ኑ፥ ሌሊቱን ሁሉ በማቅ ላይ ተኙ።
ለሠራዊት ጌታ ቤት ካህናት ለነቢያትም፦ “ለብዙ ዓመታት እንዳደረግሁት በአምስተኛው ወር መጾምና ማልቀስ ይገባኛልን?” ብለው እንዲናገሩ ልኳቸው ነበር።
ለምድሩ ሕዝብና ለካህናት ለሁሉም እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ በዚህ በሰባው ዓመት በአምስተኛውና በሰባተኛው ወር ስትጾሙና ስታለቅሱ፥ በውኑ ለእኔ ነው የጾማችሁልኝ?
ነገር ግን አስቀድሜ በደማስቆ ላሉት በኢየሩሳሌምም በይሁዳም አገር ሁሉ ለአሕዛብም ንስሓ ይገቡ ዘንድና ለንስሓ የሚገባ ነገር እያደረጉ ወደ እግዚአብሔር ይመለሱ ዘንድ ተናገርሁ።
የእስራኤልም ሕዝብ ሁሉ ወደ ቤቴል ወጡ፤ እዚያም እያለቀሱ በጌታ ፊት ተቀመጡ፤ በዚያን ቀን እስኪመሽ ድረስ ጾሙ፤ በጌታ ፊት የሚቃጠል መሥዋትና የኅብረት መሥዋዕት አቀረቡ።
ሳሙኤልም የእስራኤልን ቤት ሁሉ፥ “በፍጹም ልባችሁ ወደ ጌታ የምትመለሱ ከሆነ፥ ባዕዳን አማልክትና አስታሮትን ከመካከላችሁ አስወግዱ፤ ራሳችሁንም ለጌታ አሳልፋችሁ ስጡ፤ እርሱንም ብቻ አምልኩ፤ እርሱም ከፍልስጥኤማውያን እጅ ይታደጋችኋል።” አላቸው።
እስራኤላውያን በምጽጳ በተሰበሰቡ ጊዜ፥ ውሃ ቀድተው በጌታ ፊት አፈሰሱ፤ በዚያች ዕለትም ጾሙ፤ በዚያም “እግዚአብሔርን በድለናል” አሉ። ሳሙኤልም በምጽጳ እስራኤልን ይፈርድ ነበር።