ዘፀአት 37:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባስልኤል ከግራር እንጨት ታቦቱን ሠራ፤ ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፥ ወርዱ አንድ ክንድ ተኩል፥ ቁመቱም አንድ ክንድ ተኩል ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባስልኤል ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፣ ወርዱ አንድ ክንድ ተኩል፣ ከፍታው አንድ ክንድ ተኩል የሆነ ታቦት ከግራር ዕንጨት ሠራ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባጽልኤልም ከግራር እንጨት የቃል ኪዳኑን ታቦት ሠራ፤ ርዝመቱ መቶ ዐሥር ሳንቲ ሜትር፥ የጐኑ ስፋት ሥልሳ ስድስት ሳንቲ ሜትር፥ ቁመቱም ሥልሳ ስድስት ሳንቲ ሜትር ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባስልኤልም ከማይነቅዝ ዕንጨት ታቦትን ሠራ፤ ርዝመቷ ሁለት ክንድ ተኩል፥ ወርድዋ አንድ ክንድ ተኩል፥ ቁመቷም አንድ ክንድ ተኩል ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባስልኤልም ከግራር እንጨት ታቦቱን ሠራ፤ ርዝመቱም ሁለት ክንድ ተኩል፥ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል፥ ቁመቱም አንድ ክንድ ተኩል ነበር። |
መጋረጃውንም ከመያዣዎቹ በታች ታንጠለጥለዋለህ፥ በመጋረጃውም ውስጥ የምስክርን ታቦት አግባው፤ መጋረጃውም በቅድስቱና በቅድስተ ቅዱሳኑ መካከል መለያ ይሁናችሁ።
በዚያም ውስጥ የወርቅ ማዕጠንት ነበር፤ ሁለንተናዋም በወርቅ የተለበጠች የኪዳን ታቦት፥ በእርስዋም ውስጥ መና ያለባት የወርቅ መሶብና የበቀለች የአሮን በትር የኪዳኑም ጽላት ነበሩ።