2 ሳሙኤል 2:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህ በኋላ ዳዊት፥ “ከይሁዳ ከተሞች ወደ አንዲቱ ልውጣን?” ብሎ ጌታን ጠየቀ። ጌታም፥ “አዎን ውጣ” አለው። ዳዊትም፥ “ወደ የትኛዪቱ ልሂድ?” ሲል ጠየቀ። እርሱም፥ “ወደ ኬብሮን” ብሎ መለሰለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ ዳዊት፣ “ከይሁዳ ከተሞች ወደ አንዲቱ ልውጣን?” ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም፣ “አዎን ውጣ” አለው። ዳዊትም፣ “ወደ የትኛዪቱ ልሂድ?” ሲል ጠየቀ። እግዚአብሔርም፣ “ወደ ኬብሮን” ብሎ መለሰለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ዳዊት ከይሁዳ ከተሞች ወደ አንድዋ ልውጣን? ሲል እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም “አዎ ውጣ” አለው። ዳዊትም “ወደ የትኛይቱ ከተማ ልሂድ?” ሲል ጠየቀ። እግዚአብሔርም “ወደ ኬብሮን ከተማ ሂድ” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚያም በኋላ ዳዊት፥ “ከይሁዳ ከተሞች ወደ አንዲቱ ልውጣን?” ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም፥ “ውጣ” አለው። ዳዊትም፥ “ወዴት ልውጣ?” አለ። እርሱም፥ “ወደ ኬብሮን ውጣ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚያም በኋላ ዳዊት፦ ከይሁዳ ከተሞች ወደ አንዲቱ ልውጣን? ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ። እግዚአብሔርም፦ ውጣ አለው። ዳዊትም፦ ወዴት ልውጣ? አለ። እርሱም፦ ወደ ኬብሮን ውጣ አለው። |
ስለዚህም ዳዊት ጌታን፥ “ፍልስጥኤማውያንን ወጥቼ ልውጋቸው? በእጄስ አሳልፈህ ትሰጠኛለህ?” ሲል ጠየቀ። ጌታም፥ “ሂድ፤ በእርግጥ ፍልስጥኤማውያንን በእጅህ አሳልፌ እሰጥሃለሁ” አለው።
ለእግዚአብሔርም ቤት አገልግሎት አምስት ሺህ መክሊት ወርቅና ዐሥር ሺህ ዳሪክ፥ ዐሥር ሺህም መክሊት ብር፥ ዐሥራ ስምንት ሺህም መክሊት ናስ፥ መቶ ሺህም መክሊት ብረት ሰጡ።
ጌታን አንዲት ነገር ለመንሁት እርሷንም እሻለሁ፥ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በጌታ ቤት እኖር ዘንድ፥ ጌታን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ፥ መቅደሱንም እመለከት ዘንድ።
በደቡብም በኩል ወጡ፥ ወደ ኬብሮንም ደረሱ፤ በዚያም የዔናቅ ልጆች አኪመን፥ ሴሲ፥ ተላሚ ነበሩ። ኬብሮንም በግብጽ ካለችው ከጣኔዎእ ከሰባት ዓመት በፊት የተቈረቈረች ከተማ ነበረች።
በካህኑም በአልዓዛር ፊት ይቁም፤ እርሱም በጌታ ፊት በኡሪም ፍርድ ይጠይቅለት፤ እርሱ ከእርሱም ጋር የእስራኤል ልጆች ማኅበሩም ሁሉ በቃሉ ይውጡ፥ በቃሉም ይግቡ።”
ጌታም ኢያሱን እንዳዘዘው ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ በይሁዳ ልጆች መካከል ቂርያት-አርባቅ የምትባለውን ከተማ ድርሻ አድርጎ ሰጠው፤ እርሷም ኬብሮን ናት፥ ይህም አርባቅ የዔናቅ አባት ነበረ።
እርሱም፥ “እነዚህን ፍልስኤማውያን ሄጄ ልምታን?” ሲል ጌታን ጠየቀ። ጌታም፥ “ሂድ፤ ፍልስጥኤማውያንን ምታ፤ ቅዒላንም አድናት” ብሎ መለሰለት።