Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ዜና መዋዕል 11:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ጾርዓን፥ ኤሎንን፥ ኬብሮንን ሠራ፤ እነዚህም የተመሸጉ ከተሞች በይሁዳና በብንያም የሚገኙ ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ጾርዓ፣ ኤሎን፣ ኬብሮን ናቸው። በይሁዳና በብንያም ውስጥ የተመሸጉት ከተሞች እነዚህ ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ጾርዓ፥ አያሎንና ኬብሮን ተብለው የሚጠሩት ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ሶር​ዓን፥ ኤሎ​ንን፥ ኬብ​ሮ​ንን ሠራ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ጾርዓን፥ ኤሎንን፥ ኬብሮንን ሠራ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ዜና መዋዕል 11:10
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዳዊት በኬብሮን ነግሶ እስራኤልን የገዛው ሰባት ዓመት ከስድስት ወር ነበረ።


በንፍታሌም ባለው በተራራማው አገር በገሊላ ቃዴስን፥ በኤፍሬምም ባለው በተራራማው አገር ሴኬምን፥ በይሁዳም ባለው በተራራማው አገር ኬብሮን የምትባለውን ቂርያት-አርባቅን ለዩ።


በቈላው ኤሽታኦል፥ ጾርዓ፥ አሽና፥


ስለዚህም የእስራኤል አምላክ ጌታን ፈጽሞ ስለ ተከተለ ኬብሮን እስከ ዛሬ ለቄኔዛዊው ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ ርስት ሆነች።


በደቡብም በኩል ወጡ፥ ወደ ኬብሮንም ደረሱ፤ በዚያም የዔናቅ ልጆች አኪመን፥ ሴሲ፥ ተላሚ ነበሩ። ኬብሮንም በግብጽ ካለችው ከጣኔዎእ ከሰባት ዓመት በፊት የተቈረቈረች ከተማ ነበረች።


በከነዓንም ምድር ባለችው ቂርያት-አርባዕ ተብላ በምትጠራው በኬብሮን ከተማ ሞተች፤ አብርሃምም ለሣራ ሊያዝንላትና ሊያለቅስላት ተነሣ።


ጌታም በእስራኤል ልጆች እጅ አሞራውያንን አሳልፎ በሰጠ ቀን ኢያሱ ለጌታ እንዲህ ብሎ ተናገረ፤ የእስራኤልም ልጆች እያዩ እንዲህ አለ፦ “በገባዖን ላይ ፀሐይ ትቁም፥ በኤሎንም ሸለቆ ጨረቃ፤”


ኢያሱም ከእርሱም ጋር እስራኤል ሁሉ ከዔግሎም ወደ ኬብሮን ወጡ፥ ወጉአትም፥


አዶራይምን፥ ለኪሶን፥ ዓዜቃን፥


ምሽጎቹንም አጠነከረ፥ አዛዦችንም አኖረባቸው፥ ምግቡንም ዘይቱንም የወይን ጠጁንም አከማቸባቸው።


ጌታም ኢያሱን እንዳዘዘው ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ በይሁዳ ልጆች መካከል ቂርያት-አርባቅ የምትባለውን ከተማ ድርሻ አድርጎ ሰጠው፤ እርሷም ኬብሮን ናት፥ ይህም አርባቅ የዔናቅ አባት ነበረ።


ከዚህ በኋላ ዳዊት፥ “ከይሁዳ ከተሞች ወደ አንዲቱ ልውጣን?” ብሎ ጌታን ጠየቀ። ጌታም፥ “አዎን ውጣ” አለው። ዳዊትም፥ “ወደ የትኛዪቱ ልሂድ?” ሲል ጠየቀ። እርሱም፥ “ወደ ኬብሮን” ብሎ መለሰለት።


ደግሞም ፍልስጤማውያን በቈላውና በደቡብ በኩል ባሉት በይሁዳ ከተሞች አደጋ ጥለው ነበር፤ ቤትሳሚስንና ኤሎንን፥ ግዴሮትንም፥ ሦኮንና መንደሮችዋን፥ ተምናንና መንደሮችዋን፥ ጊምዞንና መንደሮችዋን ወስደው በዚያ ተቀምጠው ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች