2 ሳሙኤል 14:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ሴቲቱ፥ “እኔ አገልጋይህ ለጌታዬ ለንጉሡ አንዲት ቃል እንድናገር ፍቀድልኝ” አለችው። እርሱም፥ “ተናገሪ” አላት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ሴቲቱ፣ “እኔ አገልጋይህ ለጌታዬ ለንጉሡ አንዲት ቃል እንድናገር ፍቀድልኝ” አለችው። እርሱም፣ “ዕሺ ተናገሪ” አላት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሴቲቱም “ንጉሥ ሆይ! እንደገናም እኔ አገልጋይህ አንድ ነገር እንድናገር ፍቀድልኝ” አለችው። እርሱም “እሺ ተናገሪ” አላት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሴቲቱም፥ “እኔ አገልጋይህ ለጌታዬ ለንጉሥ አንድ ቃል ልናገር” አለች፤ እርሱም፥ “ተናገሪ” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሴቲቱም፦ እኔ ባሪያህ ለጌታዬ ለንጉሥ አንድ ቃል ልናገር አለች፥ እርሱም፦ ተናገሪ አለ። |
እርሱም፦ “እኔ ደግሞ አንድ ጊዜ ብቻ ብናገር ጌታዬ አይቆጣ፥ ምናልባት ከዚያ ዐሥር ቢገኙሳ?” አለ። እርሱም፦ “ስለ አሥሩ አላጠፋትም” አለ።
ይሁዳም ወደ ዮሴፍ ቀረብ ብሎ፥ “ጌታዬ ሆይ፤ እኔ አገልጋይህ አንዲት ቃል ብቻ ልናገር፤ አንተም የፈርዖን ያህል የተከበርህ ስለሆንህ፥ እባክህን እኔን አገልጋይህን አትቈጣኝ።
እርሷም፥ “ደም ተበቃዮቹ ተጨማሪ ደም እንዳያፈሱ ልጄም እንዳይገደል፥ ንጉሡ ጌታ አምላኩን ያስብ” አለች። ንጉሡም፥ “ሕያው በሆነው ጌታ እምላለሁ! ከልጅሽ አንድ ጠጉር በምድር ላይ አይወድቅም” አላት።
ሴቲቱም እንዲህ አለችው፥ “አንተስ እንዲህ ያለውን ነገር በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ያሰብኸው ለምንድን ነው? ከአገር የተሰደደውን ልጁን ንጉሡ ባለመመለሱ፥ ይህን ሲናገር በራሱ ላይ መፍረዱ አይደለምን?
ኢዮአብ ወደ እርሷ ቀረበ፤ እርሷም፥ “ኢዮአብ አንተ ነህ?” ስትል ጠየቀችው። እርሱም፥ “አዎን እኔ ነኝ” ብሎ መለሰላት። እርሷም፥ “እንግዲህ አገልጋይህ የምትለውን አድምጥ” አለችው። እርሱም፥ “እያዳመጥኩ ነው” አላት።
አቤቱ! ከአንተ ጋር በተምዋገትሁ ጊዜ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ነገር ግን ከአንተ ጋር ስለ ፍርድ ልናገር። የኃጢአተኞች መንገድ ስለምን ይቃናል? በደልንስ ለሚበድሉ ሁሉ ስለምን ደኅንነት ይሆናል?