Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 18:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 አብርሃምም መለሰ ዓለም፦ “እኔ አፈርና አመድ ስሆን ከጌታዬ ጋር እናገር ዘንድ እነሆ አንድ ጊዜ ጀመርሁ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ደግሞም አብርሃም እንዲህ አለ፤ “እኔ ከንቱ፣ ትቢያና ዐመድ ሆኜ ሳለሁ ከጌታ ጋራ ለመናገር አንዴ ደፍሬአለሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 አብርሃም እንደገና እንዲህ አለ፤ “እኔ ትቢያና ዐመድ የሆንኩ ከንቱ ሰው፥ ከጌታዬ ጋር በድፍረት በመነጋገሬ ይቅር በለኝ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 አብ​ር​ሃ​ምም መለሰ፤ አለም፥ “እኔ አፈ​ርና አመድ ስሆን ከጌ​ታዬ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር እና​ገር ዘንድ አሁን ጀመ​ርሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 አብርሃምም መለስን አለም፤ እኔ አፈርና አመድ ስሆን ከጌታዬ ጋር እናገር ዘንድ እነሆ አንድ ጊዜ ጀመርሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 18:27
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እኔም፤ “ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው ነኝ፤ የምኖረውም ከንፈሮቹ በረከሱበት ሕዝብ መካከል ነው፤ ዐይኖቼም ንጉሡን፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን አይቷልና ጠፍቻለሁ፤ ወዮልኝ!” አልሁ።


ስምዖን ጴጥሮስም ይህን ባየ ጊዜ በኢየሱስ ጉልበት ፊት ወድቆ፦ “ጌታ ሆይ! እኔ ኀጢአተኛ ሰው ነኝና ከኔ ራቅ፤” አለው።


“ወደ ወጣህበት መሬት እስክትመለስ ድረስ በግንባርህ ላብ እንጀራን ትበላለህ፥ አፈር ነህና፥ ወደ አፈርም ትመለሳለህ።”


ሳይታክቱም ዘወትር ሊጸልዩ እንደሚገባቸው የሚያስተምር ምሳሌን ነገራቸው፤


አሁን ግን፥ አቤቱ ጌታ፥ አንተ አባታችን ነህ፤ እኛ ጭቃ ነን፤ አንተም ሠሪያችን ነህ፥ እኛም ሁላችን የእጅህ ሥራ ነን።


አፈርም ወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ፥ ነፍስም ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ ፈጣሪህን አስብ።


በጭቃ ውስጥ ጣለኝ፥ አፈርና አመድም መሰልሁ።


ይልቁንስ በጭቃ ቤት የሚኖሩ፥ መሠረታቸው በትቢያ ውስጥ የሆነ፥ ከብል በፊት የሚጨፈለቁ እንዴት ይሆኑ?


ከዚህ በኋላ ጌታ እግዚአብሔር ሰውን ከምድር አፈር አበጀው፥ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት፥ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።


አቤቱ፥ እርሱን ታውቀው ዘንድ ሰው ምንድነው? ታስብለት ዘንድ የሰው ልጅ ምንድነው?


የጣቶችህን ሥራ ሰማዮችህን ባየሁ ጊዜ፥ ጨረቃንና ከዋክብትን አንተ የሠራሃቸውን፥


እንዲህም አልሁ፦ “አምላኬ ሆይ፥ አፍሬአለሁ፤ አምላኬ ሆይ፥ ፊቴንም ወደ አንተ ለማንሣት እፈራለሁ፥ ኃጢአታችን ከራሳችን በላይ ከፍ ብሏልና፥ በደላችንም ወደ ሰማያት ወጥቷልና።


ከአምሳው ጻድቃን አምስት ቢጐድሉ ከተማይቱን ሁሉ በአምስቱ ምክንያት ታጠፋለህን?” “ከዚያ አርባ አምስት ባገኝ አላጠፋትም” አለ።


ሙሴም በጌታ አምላኩ ፊት ለመነ፥ እንዲህም አለ፦ “ጌታ ሆይ በታላቅ ኃይልና በጽኑ እጅ ከግብጽ ምድር ባወጣኸው በሕዝብህ ላይ ቁጣህ ስለምን ነደደ?


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች