ይህ ሰው ከጥቂት ጊዜ በፊት በጭካኔ አስተሳሰቡ የባሕርን ማዕበል ማዘዝ እንኳ የሚችል መስሎ ይታየው፥ የተራሮችን ጫፍ መመዘን፥ ክብደታቸውን ለማሳወቅ የሚችል አድርጐ ራሱን ይቆጥር የነበረ፥ አሁን ግን መሬት ላይ ተጋድሞ በቃሬዛ ተሸክመው ወሰዱት። የእግዚአብሔርን ታላቅነት ሁሉም ማወቅ ቻሉ።