ከጢሞቴዎስና ከባቂደስ ወታደሮች ጋር ተዋግተው ከሃያ ሺህ የሚበዙ ሰዎችን ገደሉ፤ ረዣዥም ምሽጐችንም ያዙ፤ የማረኩትንም ብዙ ምርኮ በሁለት ከፍለው ግማሹን እነርሱ ወሰዱት፤ የቀረውን ግማሽ ለስደተኞች፤ ለሙት ልጆች፥ ለመበለቶችና ለሸማግሌዎች አከፋፈሉ።