ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ኢዩን “በአክዓብ ተወላጆች ሁሉ ላይ ልታደርግ የሚገባህን ባዘዝኩህ መሠረት ፈጽመሃል፤ ከዚህም የተነሣ የአንተ ትውልድ እስከ አራት ትውልድ ድረስ በእስራኤል ላይ እንደሚነግሡ የተስፋ ቃል እሰጥሃለሁ” አለው።
2 ነገሥት 14:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የኢዮአስ ልጅ አሜስያስ በይሁዳ በነገሠ በዐሥራ አምስተኛው ዓመት የዮአስ ልጅ ኢዮርብዓም በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ እርሱም መኖሪያውን በሰማርያ አድርጎ አርባ አንድ ዓመት ገዛ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኢዮአስ ልጅ አሜስያስ በይሁዳ በነገሠ በዐሥራ ዐምስተኛው ዓመት፣ የእስራኤል ንጉሥ የዮአስ ልጅ ኢዮርብዓም በሰማርያ ነገሠ፤ አርባ አንድ ዓመትም ገዛ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የኢዮአስ ልጅ አሜስያስ በይሁዳ በነገሠ በዐሥራ አምስተኛው ዓመት የዮአስ ልጅ ኢዮርብዓም በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ አርሱም መኖሪያውን በሰማርያ አድርጎ አርባ አንድ ዓመት ገዛ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በይሁዳ ንጉሥ በኢዮአስ ልጅ በአሜስያስ በዐሥራ አምስተኛው ዓመተ መንግሥት የእስራኤል ንጉሥ የዮአስ ልጅ ኢዮርብዓም በሰማርያ መንገሥ ጀመረ፤ አርባ አንድ ዓመትም ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በይሁዳ ንጉሥ በኢዮአስ ልጅ በአሜስያስ በዐሥራ አምስተኛው ዓመት የእስራኤል ንጉሥ የዮአስ ልጅ ኢዮርብዓም በሰማርያ መንገሥ ጀመረ፤ አርባ አንድ ዓመትም ነገሠ። |
ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ኢዩን “በአክዓብ ተወላጆች ሁሉ ላይ ልታደርግ የሚገባህን ባዘዝኩህ መሠረት ፈጽመሃል፤ ከዚህም የተነሣ የአንተ ትውልድ እስከ አራት ትውልድ ድረስ በእስራኤል ላይ እንደሚነግሡ የተስፋ ቃል እሰጥሃለሁ” አለው።
ንጉሥ ዮአስ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ እንዲሁም በይሁዳ ንጉሥ በአሜስያስ ላይ ባደረገው ጦርነት የፈጸመው የጀግንነት ሥራ ጭምር በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል።
ዳግማዊ ኢዮርብዓምም እስራኤልን ወደ ኃጢአት የመራ ከእርሱ በፊት የነበረውን የናባጥ ልጅ የኢዮርብዓምን መጥፎ አርአያነት በመከተል ኃጢአት በመሥራቱ እግዚአብሔርን አሳዘነ።
ይሁን እንጂ እነርሱ ለዘለዓለም ፈጽሞ እንዲደመሰሱ ደግሞ የእግዚአብሔር ፈቃድ አልነበረም፤ ስለዚህም በዳግማዊ ኢዮርብዓም አማካይነት አዳናቸው።
በይሁዳ ነገሥታት በዖዝያንና በኢዮአታም፥ በአካዝና በሕዝቅያስም ዘመን፥ በእስራኤልም ንጉሥ በዮአስ ልጅ በኢዮርብዓም ዘመን፥ ወደ ብኤሪ ልጅ ወደ ሆሴዕ የመጣው የጌታ ቃል ይህ ነው።
የአሞጽ ቃላት፥ በቴቁሔ ከሚገኙ ከበግ አርቢዎች መካከል የነበረ፥ በይሁዳ ንጉሥ በዖዝያን ዘመን፥ በእስራኤልም ንጉሥ በዮአስ ልጅ በኢዮርብዓም ዘመን፥ የምድር መናወጥ ከመሆኑ ከሁለት ዓመት በፊት ስለ እስራኤል ያየው ይህ ነው።