Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 14:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ዖዝያም ቀድሞ ተይዛ የነበረችውን ኤላትን ከአባቱ ሞት በኋላ በጦር ኃይል ድል ነሥቶ በማስመለስ እንደገና ሠራት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ንጉሥ አሜስያስ ከአባቶቹ ጋራ ካንቀላፋ በኋላ ኤላትን እንደ ገና ሠርቶ ወደ ይሁዳ የመለሳት ይኸው ዓዛርያስ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ዖዝያም ቀድሞ ተይዛ የነበረችውን ኤላትን ከአባቱ ሞት በኋላ በጦር ኀይል ድል ነሥቶ በማስመለስ እንደገና ሠራት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ንጉ​ሡም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር ከአ​ን​ቀ​ላፋ በኋላ፥ ኤላ​ትን ሠርቶ ወደ ይሁዳ መለ​ሳት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ንጉሡም ከአባቶቹ ጋር ካንቀላፋ በኋላ፥ ኤላትን ሠርቶ ወደ ይሁዳ መለሳት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 14:22
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እንዲሁም ንጉሥ ሰሎሞን በኤዶም ምድር በቀይ ባሕር ዳርቻ በምትገኘው በኤላት አጠገብ ባለችው በዔጽዮንጋብር መርከቦችን ሠራ።


የይሁዳም ሕዝብ ዐሥራ ስድስት ዓመት ዕድሜ የነበረውን ልጁን ዖዝያን አነገሡ፤


የኢዮአስ ልጅ አሜስያስ በይሁዳ በነገሠ በዐሥራ አምስተኛው ዓመት የዮአስ ልጅ ኢዮርብዓም በእስራኤል ላይ ነገሠ፤ እርሱም መኖሪያውን በሰማርያ አድርጎ አርባ አንድ ዓመት ገዛ።


በዚያኑ ጊዜ የሶርያ ንጉሥ ረጺን የኤላትን ከተማ አስመልሶ በቁጥጥሩ ሥር በማድረግ በዚያ የነበሩትን አይሁድ አስወጣ፤ ያንጊዜ በኤላት የሰፈሩት ኤዶማውያን እስከ አሁን በዚያ ይገኛሉ።


ንጉሡም ከአባቶቹ ጋር ከአንቀላፋ በኋላ ዖዝያን ኤላትን ሠራ፥ ወደ ይሁዳም መለሳት።


ሰሎሞንም የዚያን ጊዜ በኤዶምያስ ምድር በባሕር ዳር ወዳሉ ወደ ዔጽዮን-ጋብርና ወደ ኤሎት ሄደ።


“እኛም ወንድሞቻችን የዔሳው ልጆች ከተቀመጡት ሴይር አልፈን፥ በዓረባ መንገድ ከኤላትና ከዔጽዮንጋብር አለፍን። ተመልሰንም በሞዓብ ምድረ በዳ መንገድ አለፍን።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች