ዘሌዋውያን 25:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)33 ማናቸውም ሰው ከሌዋውያን ቢገዛ፥ በእስራኤል ልጆች መካከል የሌዋውያን ከተሞች ቤቶች ርስቶቻቸው ናቸውና በርስቱ ከተማ ያለ የተሸጠው ቤት በኢዮቤልዩ ዓመት ይመለሳል። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም33 ሌዋውያን በከተማቸው ያለውን ቤታቸውን ቢሸጡና መዋጀት ባይችሉ፣ በኢዮቤልዩ ይመለሳል፤ በሌዋውያን ከተሞች የሚገኙ ቤቶች በእስራኤላውያን መካከል የሌዋውያን ንብረት ናቸውና። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)33 ማናቸውም ሰው ከሌዋውያን ቤት ቢገዛ፥ በእስራኤል ልጆች መካከል በሌዋውያን ከተሞች ያሉ ቤቶች ለሌዋውያን ርስቶቻቸው ናቸውና በርስታቸው ከተማ ውስጥ የተሸጠው ቤት በኢዮቤልዩ ይመለሳል። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም33 ሌዋውያን በገዛ ከተሞቻቸው የሚሠሩአቸው ቤቶች በእስራኤላውያን መካከል የእነርሱ ቀዋሚ ንብረቶች ናቸው። በእነዚህ ከተሞች ውስጥ አንድ ሌዋዊ ቤት ቢሸጥና መልሶ ለመዋጀት ባይችል በኢዮቤልዩ ዓመት ይመለስለታል፤ Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)33 ማናቸውም ሰው ከሌዋውያን ቤት ቢገዛ፥ በእስራኤል ልጆች መካከል የሌዋውያን ከተማ ቤቶች ርስቶቻቸው ናቸውና በርስቱ ከተማ ያለ የተሸጠው ቤት በኢዮቤልዩ ይመለሳል። Ver Capítulo |