Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መሳፍንት 16:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ደሊ​ላም አስ​ተ​ኛ​ችው፤ የራ​ሱ​ንም ጠጕር ሰባ​ቱን ጕን​ጕን ከድር ጋር ጐነ​ጐ​ነ​ችው፤ በግ​ድ​ግ​ዳም ላይ በች​ካል ቸከ​ለ​ቻ​ቸው፥ “ሶም​ሶን ሆይ! ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን መጡ​ብህ” አለ​ችው። ከእ​ን​ቅ​ል​ፉም ነቃ፥ ችካ​ሉ​ንም ከነ​ቈ​ን​ዳ​ላው ከግ​ድ​ግ​ዳው ነቀለ፤ ኀይ​ሉም አል​ታ​ወ​ቀም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ከችካልም ጋራ ቸከለችው። እንደ ገናም፣ “ሳምሶን! ፍልስጥኤማውያን መጡብህ” አለችው። ሳምሶን ከእንቅልፉ ነቃ፤ ችካሉን ከነድሩ፣ ከነሹሩባው ነቀለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ደሊላም መተኛቱን አይታ ሰባቱን ቈንዳላዎቹን ከድር ጋር ጐነጐነችው፤ ከችካልም ጋር ቸከለችው። እንደገናም፥ “ሳምሶን ፍልስጥኤማውያን መጡብህ” አለችው። ሳምሶን ከእንቅልፉ ነቃ፤ ችካሉን ከነድሩ፥ ከነቈንዳላው ነቀለው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ከዚህ በኋላ ደሊላ ተኝቶ ሳለ የራሱን ጠጒር ሰባቱን ቁንዳላዎች ከድር ጋር ጐንጒና በችካል ቸከለችው፤ ከዚያ በኋላ “ሶምሶን! ፍልስጥኤማውያን መጡብህ!” ብላ ጮኸች፤ እርሱ ግን ከእንቅልፉ ነቅቶ ጠጒሩን ከችካሉና ከድሩ ላይ ነቀለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ሶምሶንም በተኛ ጊዜ ደሊላ የራሱን ጠጉር ሰባቱን ጉንጉን ከድሩ ጋር ጐነጐነችው፥ በችካልም ቸከለችውና፦ ሶምሶን ሆይ፥ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ አለችው። ከእንቅልፉም ነቃ፥ ችካሉንም ከነቆንዳላው ድሩንም ነቀለ።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 16:14
4 Referencias Cruzadas  

ይህን የሚ​ጠ​ብቅ ጥበ​በኛ ማን ነው? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅር ባይ እንደ ሆነ ያው​ቃል።


ደሊ​ላም ሶም​ሶ​ንን፥ “እስከ አሁን ድረስ አታ​ለ​ል​ኸኝ፤ የነ​ገ​ር​ኸ​ኝም ሐሰት ነው፤ የም​ት​ታ​ሰ​ር​በት ምን እን​ደ​ሆነ ንገ​ረኝ” አለ​ችው። እር​ሱም፥ “የራ​ሴን ጠጕር ሰባ​ቱን ጕን​ጕን ከድር ጋር ብት​ጐ​ነ​ጕ​ኚው፥ በግ​ድ​ግ​ዳም ላይ በች​ካል ብት​ቸ​ክ​ዪው፥ ከሰ​ዎች እንደ አንዱ እደ​ክ​ማ​ለሁ፥” አላት።


ደሊ​ላም፥ “ ‘አንተ እወ​ድ​ድ​ሻ​ለሁ’ እን​ዴት ትለ​ኛ​ለህ? ልብህ ከእኔ ጋር አይ​ደ​ለም፤ ስታ​ታ​ል​ለኝ ይህ ሦስ​ተኛ ጊዜህ ነው፥ ታላቅ ኀይ​ል​ህም በምን እንደ ሆነ አል​ነ​ገ​ር​ኸ​ኝም” አለ​ችው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos