መሳፍንት 16:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 ደሊላም መተኛቱን አይታ ሰባቱን ቈንዳላዎቹን ከድር ጋር ጐነጐነችው፤ ከችካልም ጋር ቸከለችው። እንደገናም፥ “ሳምሶን ፍልስጥኤማውያን መጡብህ” አለችው። ሳምሶን ከእንቅልፉ ነቃ፤ ችካሉን ከነድሩ፥ ከነቈንዳላው ነቀለው። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 ከችካልም ጋራ ቸከለችው። እንደ ገናም፣ “ሳምሶን! ፍልስጥኤማውያን መጡብህ” አለችው። ሳምሶን ከእንቅልፉ ነቃ፤ ችካሉን ከነድሩ፣ ከነሹሩባው ነቀለው። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 ከዚህ በኋላ ደሊላ ተኝቶ ሳለ የራሱን ጠጒር ሰባቱን ቁንዳላዎች ከድር ጋር ጐንጒና በችካል ቸከለችው፤ ከዚያ በኋላ “ሶምሶን! ፍልስጥኤማውያን መጡብህ!” ብላ ጮኸች፤ እርሱ ግን ከእንቅልፉ ነቅቶ ጠጒሩን ከችካሉና ከድሩ ላይ ነቀለው። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 ደሊላም አስተኛችው፤ የራሱንም ጠጕር ሰባቱን ጕንጕን ከድር ጋር ጐነጐነችው፤ በግድግዳም ላይ በችካል ቸከለቻቸው፥ “ሶምሶን ሆይ! ፍልስጥኤማውያን መጡብህ” አለችው። ከእንቅልፉም ነቃ፥ ችካሉንም ከነቈንዳላው ከግድግዳው ነቀለ፤ ኀይሉም አልታወቀም። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 ሶምሶንም በተኛ ጊዜ ደሊላ የራሱን ጠጉር ሰባቱን ጉንጉን ከድሩ ጋር ጐነጐነችው፥ በችካልም ቸከለችውና፦ ሶምሶን ሆይ፥ ፍልስጥኤማውያን መጡብህ አለችው። ከእንቅልፉም ነቃ፥ ችካሉንም ከነቆንዳላው ድሩንም ነቀለ። Ver Capítulo |