40 በዋሾቻቸው ውስጥ ተጋድመው በጫካም ውስጥ አድብተው ይቀመጣሉና።
40 እነርሱ በዋሻ ውስጥ ያደባሉ፤ በደን ውስጥም ይጋደማሉ።
40 የተራቡ ልጆችዋንስ መመገብ ትችላለህን?
ይሁዳ የአንበሳ ደቦል ነው፤ ልጄ ሆይ፥ ከመሰማሪያህ ወጣህ፤ እንደ አንበሳ ተኛህ፤ አንቀላፋህም፤ እንደ አንበሳም ደቦል የሚቀሰቅስህ የለም።
አውሬዎቹም ወደ ጫካው ይገባሉ፥ በዋሾቻቸውም ያርፋሉ።
ልጆቹ ወደ እግዚአብሔር ሲጮኹ፥ የሚበሉትም ፈልገው ሲቅበዘበዙ፥ ለቍራ መብልን የሚሰጠው ማን ነው?
እነሆ፥ ሕዝቡ እንደ አንበሳ ደቦል ያገሣል፤ እንደ አንበሳም ይነሣል፤ ያደነውን እስኪበላ፥ የገደለውንም ደሙን እስኪጠጣ አይተኛም።”
አርፎአል፥ እንደ አንበሳና እንደ አንበሳ ደቦል ተጋድሞአል፤ ማን ያስነሣዋል? የሚመርቁህ ሁሉ የተመረቁ ይሁኑ፤ የሚረግሙህም ሁሉ የተረገሙ ይሁኑ።”