40 የተራቡ ልጆችዋንስ መመገብ ትችላለህን?
40 እነርሱ በዋሻ ውስጥ ያደባሉ፤ በደን ውስጥም ይጋደማሉ።
40 በዋሾቻቸው ውስጥ ተጋድመው በጫካም ውስጥ አድብተው ይቀመጣሉና።
ይሁዳ እንደ ደቦል አንበሳ ነው፤ ልጄ መብል የሚሆነውን አድኖ፥ ወደ ዋሻው ይመለሳል፤ እንደ አንበሳ ተዝናንቶ ይተኛል፤ ሊቀሰቅሰው የሚደፍር ማነው?
በዚያን ጊዜ የዱር አውሬዎች ሸሽተው ወደየመሸሸጊያቸው ይገባሉ፤ በየዋሻቸውም ውስጥ ይሰወራሉ።
ልጆችዋ ምግብ አጥተው ሲቅበዘበዙ ወደ እኔም ሲጮኹ ለቁራ ምግብ የሚሰጣት ማነው?”
እርሱም እንደ አንበሳ ተደብቆ ይቈያል፤ ድኾችን ለመያዝ ይሸምቃል፤ እነርሱንም በአሽክላው ይዞ ይጐትታቸዋል።
የእስራኤል ሕዝብ እንደ እንስት አንበሳ ይቆማል፤ እንደ አንበሳም ይነሣል፤ ያደነውን ሳይበላና ደሙን ሳይጠጣ አያርፍም።”
ይህ ሕዝብ፥ ለመያዝ እንደ ተዘጋጁ ወንድ አንበሳና ሴት አንበሳ አድብቶአል፤ በተኛ ጊዜ ሊያስነሣው የሚደፍር ማነው? የሚመርቅህ የተመረቀ ይሁን፤ የሚረግምህም የተረገመ ይሁን።”