Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢዮብ 27:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 በእ​ር​ሱም ላይ የማ​ያ​ው​ቀው ይመ​ጣ​በ​ታል፤ አይ​ራ​ራ​ለ​ትም፥ ከእ​ጁም ፈጥኖ መሸሽ ይወ​ድ​ዳል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ከነፋሱ ብርታት ለማምለጥ ይሮጣል፤ ነገር ግን እየተወረወረ ያለ ርኅራኄ ይደርስበታል፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ነፋሱ ይጥልበታል፥ አይራራለትም፥ እርሱ ግን ከእጁ ፈጥኖ ለመሸሽ ይታገላል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ሸሽቶ ለማምለጥ ቢሞክርም ነፋሱ ያለ ርኅራኄ በእርሱ ላይ ያይልበታል፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 እርሱ ይጥልበታል፥ አይራራለትም፥ ከእጁ ፈጥኖ መሸሽ ይወድዳል።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 27:22
21 Referencias Cruzadas  

ከዚህ በላይ በደ​ለኛ እን​ዳ​ል​ሆ​ንሁ፥ አንተ ታው​ቃ​ለህ። ነግር ግን ከእ​ጅህ የሚ​ያ​መ​ልጥ ማን ነው?


የኃ​ጥ​ኣን መድ​ኀ​ኒ​ታ​ቸው ታል​ቃ​ለች። ተስ​ፋ​ቸ​ው​ንም ያጣሉ፥ የዝ​ን​ጉ​ዎች ዐይ​ኖ​ችም ይጠ​ፋሉ።”


ከሰ​ይ​ፍም ኀይል አያ​መ​ል​ጥም፤ የና​ስም ቀስት ይወ​ጋ​ዋል።


በም​ድር ላይ እንደ ተፈ​ተነ፥ ሰባት ጊዜም እንደ ተጣራ ብር የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ንጹሕ ቃል ነው።


በም​ድር ሁሉ እንደ እኔ ያለ እን​ደ​ሌለ ታውቅ ዘንድ በሰ​ው​ነ​ትህ፥ በአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህም፥ በሕ​ዝ​ብ​ህም ላይ መቅ​ሠ​ፍ​ቴን ሁሉ በዚህ ጊዜ እል​ካ​ለሁ።


በተ​ጐ​በ​ኛ​ች​ሁ​በት ቀን፥ ምን ታደ​ርጉ ይሆን? መከራ ከሩቅ ይመ​ጣ​ባ​ች​ኋ​ልና፥ ለረ​ድ​ኤ​ትስ ወደ ማን ትሸ​ሻ​ላ​ችሁ?


ሰው​ንና ወን​ድ​ሙን፥ አባ​ቶ​ች​ንና ልጆ​ችን በአ​ንድ ላይ እበ​ት​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ እንጂ አል​ራ​ራ​ላ​ቸ​ውም፤ አላ​ዝ​ን​ላ​ቸ​ውም፤ አል​ም​ራ​ቸ​ው​ምም።”


እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፤ እመ​ጣ​ለሁ፤ እኔም አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ፤ አል​ተ​ውም፤ አል​ራ​ራም፤ አል​ጸ​ጸ​ትም፤ እንደ መን​ገ​ድ​ሽና እንደ ሥራ​ሽም እፈ​ር​ድ​ብ​ሻ​ለሁ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። ስለ​ዚህ የሰ​ውን ደም እንደ አፈ​ሰ​ስሽ እኔ እፈ​ር​ድ​ብ​ሻ​ለሁ፤ እንደ ኀጢ​አ​ት​ሽም ተበ​ቅዬ አጠ​ፋ​ሻ​ለሁ፤ ስም​ሽም ጐሰ​ቈለ፥ ብዙ ኀዘ​ን​ንም ታዝ​ኛ​ለሽ።”


ስለ​ዚህ እኔ ሕያው ነኝና በእ​ድ​ፍ​ሽና በር​ኵ​ሰ​ትሽ መቅ​ደ​ሴን ስላ​ረ​ከ​ስሽ፥ ስለ​ዚህ በእ​ው​ነት እኔ አሳ​ን​ስ​ሻ​ለሁ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ዐይ​ኔም አይ​ራ​ራም፤ እኔም ይቅር አል​ልም።


የሚ​ሮጥ ሰው ማም​ለጥ አይ​ች​ልም፤ ኀይ​ለ​ኛ​ውም በብ​ር​ታቱ አይ​ዝም፤ አር​በ​ኛ​ውም ነፍ​ሱን አያ​ድ​ንም።


እነ​ዚ​ያም ሰዎች ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እንደ ኰበ​ለለ እርሱ ስለ ነገ​ራ​ቸው ዐው​ቀ​ዋ​ልና እጅግ ፈር​ተው፥ “ይህ ያደ​ረ​ግ​ኸው ምን​ድን ነው?” አሉት።


ለልጁ ስንኳ አል​ራ​ራም፤ ስለ ሁላ​ችን ቤዛ አድ​ርጎ አሳ​ልፎ ሰጠው እንጂ፥ እን​ግ​ዲህ እርሱ ሁሉን እን​ዴት አይ​ሰ​ጠ​ንም?


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ፥ ቅን​አ​ቱም በዚያ ሰው ላይ ይነ​ድ​ዳል እንጂ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅ​ርታ አያ​ደ​ር​ግ​ለ​ትም፤ በዚ​ህም መጽ​ሐፍ የተ​ጻ​ፈው ርግ​ማን ሁሉ በላዩ ይኖ​ራል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስሙን ከሰ​ማይ በታች ይደ​መ​ስ​ሰ​ዋል።


ለመ​ከራ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ፍላ​ጻ​ዎ​ች​ንም እጨ​ር​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ።


ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ፊት እየ​ሸሹ በቤ​ት​ሖ​ሮን ቍል​ቍ​ለት ሲወ​ርዱ፥ ወደ ዓዜ​ቃና ወደ መቄዳ እስ​ኪ​ደ​ርሱ ድረስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰ​ማይ ታላ​ላቅ የበ​ረዶ ድን​ጋይ አወ​ረ​ደ​ባ​ቸ​ውና ሞቱ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በሰ​ይፍ ከገ​ደ​ሉ​አ​ቸው ይልቅ በበ​ረዶ ድን​ጋይ የሞ​ቱት በለጡ።


የሚ​ያ​ሳ​ድ​ድ​ህና ነፍ​ስ​ህን የሚሻ ሰው ቢነሣ፥ የጌ​ታዬ ነፍስ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በሕ​ይ​ወት ማሰ​ሪያ የታ​ሰ​ረች ትሆ​ና​ለች፤ የጠ​ላ​ቶ​ችህ ነፍስ ግን በወ​ን​ጭፍ እን​ደ​ሚ​ወ​ነ​ጨፍ ትሁን።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos