Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢዮብ 21:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ሌላ​ውም ሰው መል​ካ​ምን ነገር ከቶ ሳይ​በላ በተ​መ​ረ​ረች ነፍሱ ይሞ​ታል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ሌላው ሰው ደግሞ አንዳች መልካም ነገር ሳያይ፣ በተመረረች ነፍስ ይሞታል፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ሌላውም ሰው መልካምን ነገር ከቶ ሳይቀምስ በተመረረች ነፍስ ይሞታል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ሌሎች ግን መሪር ሐዘን ሳይለያቸው፥ በችግር እንደ ተቈራመዱ መልካም ነገር ሳያገኙ ይሞታሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ሌላውም ሰው መልካምን ነገር ከቶ ሳይቀምስ በተመረረች ነፍስ ይሞታል።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 21:25
14 Referencias Cruzadas  

ኩሲ ደግሞ አለ፥ “በሜዳ እን​ዳ​ለች አራስ ድብና እንደ ተኳር የዱር እሪያ በል​ባ​ቸው መራ​ሮ​ችና ኀያ​ላን መሆ​ና​ቸ​ውን አባ​ት​ህ​ንና ሰዎ​ቹን ታው​ቃ​ለህ፤ አባ​ትህ አር​በኛ ነው፤ ሕዝ​ቡ​ንም አያ​ሰ​ና​ብ​ትም።


ሴት​የ​ዋም፥ “አም​ላ​ክህ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! በማ​ድጋ ካለው ከእ​ፍኝ ዱቄት በማ​ሰ​ሮም ካለው ከጥ​ቂት ዘይት በቀር እን​ጀራ የለ​ኝም፤ እነ​ሆም፥ ጥቂት እን​ጨት እሰ​በ​ስ​ባ​ለሁ፤ ሄጄም ለእ​ኔና ለልጄ እጋ​ግ​ረ​ዋ​ለሁ፤ በል​ተ​ነ​ውም እን​ሞ​ታ​ለን” አለ​ችው።


“ነፍሴ ስለ ተጨ​ነ​ቀች ቃሌን በእ​ን​ጕ​ር​ጕሮ አሰ​ማ​ለሁ፤ ነፍ​ሴም እየ​ተ​ጨ​ነ​ቀች በም​ሬት እና​ገ​ራ​ለሁ።


“ሆዱን ቢያ​ጠ​ግብ፥ የመ​ዓት መቅ​ሠ​ፍት ይጨ​መ​ር​በ​ታል፤ የሕ​ማ​ሙም ሥቃይ ይጸ​ና​በ​ታል።


በው​ስጡ ስብ ሞል​ቶ​አል፥ የአ​ጥ​ን​ቶ​ቹም ቅል​ጥም ፈስ​ሶ​አል።


ሁሉም በአ​ፈር ውስጥ በአ​ንድ ላይ ይተ​ኛሉ፤ ትሎ​ችም ይሸ​ፍ​ኗ​ቸ​ዋል።


በመ​ራ​ራ​ነት ላሉት ብር​ሃን፥ በነ​ፍስ ለተ​ጨ​ነ​ቁ​ትም ሕይ​ወት፥


ስለ​ዚ​ህም እኔ አፌን አል​ከ​ለ​ክ​ልም፤ በመ​ን​ፈሴ ጭን​ቀ​ትን እና​ገ​ራ​ለሁ፤ የነ​ፍ​ሴ​ንም ምሬት በኀ​ዘን እገ​ል​ጣ​ለሁ።


እተ​ነ​ፍስ ዘንድ አይ​ተ​ወ​ኝም፤ ነገር ግን መራራ ነገ​ርን አጥ​ግ​ቦ​ኛል።


የዐዋቂ ሰው ልብ ለሰውነቱ ኀዘን ነው፤ ደስ ባለውም ጊዜ ከጥል ጋር ግንኙነት የለውም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሰው ሀብ​ት​ንና ጥሪ​ትን ክብ​ር​ንም ሰጠው፥ ከወ​ደ​ደ​ውም ሁሉ ለሰ​ው​ነቱ የከ​ለ​ከ​ላት የለም፤ ነገር ግን ሌላ ሰው ይበ​ላ​ዋል እንጂ ከእ​ርሱ ይበላ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አላ​ሠ​ለ​ጠ​ነ​ውም፤ ይህም ከን​ቱና ክፉ ደዌ ነው።


“የሰው ልጅ ሆይ! እን​ጀ​ራ​ህን በመ​ታ​ወክ ብላ፤ ውኃ​ህ​ንም በፍ​ር​ሃ​ትና በድ​ን​ጋጤ ጠጣ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos