ሕዝቅኤል 5:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 ለማጥፋትም የሆነውን፥ አጠፋችሁም ዘንድ የምሰድደውን የራብ ፍላጻ በላያችሁ በሰደድሁ ጊዜ፥ ራብን እጨምርባችኋለሁ፤ የእንጀራችሁንም በትር እሰብራለሁ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም16 የሚገድለውንና አጥፊ የሆነውን የራብ ፍላጻ በእናንተ ላይ በምወረውርበት ጊዜ በርግጥ ላጠፋችሁ እሰድዳለሁ። በራብ ላይ ራብ አመጣባችኋለሁ፤ የምግብ ምንጫችሁንም አደርቃለሁ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 የሚገድሉና የሚያጠፉ የራብ ፍላፃ በወረወርሁ ጊዜ፥ እንዳጠፋችሁ እወረውራቸዋለሁ፥ በእናንተ ላይ ረሃብን እጨምርባችኋለሁ፥ የምግባችሁንም በትር እሰብራለሁ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 እንደ ገዳይ ቀስት የሆነውን ራብ የማመጣባችሁ እንዲያጠፋችሁ ነው፤ ደጋግሜ ራብን አመጣባችኋለሁ፤ የምግብ አቅርቦታችሁም እንዲቋረጥ አደርጋለሁ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 ለማጥፋትም የሆነውን አጠፋችሁም ዘንድ የምሰድደውን የራብ ፍላፃ በላያችሁ በሰደድሁ ጊዜ ረሃብን እጨምርባችኋለሁ፥ የእንጀራችሁንም በትር እሰብራለሁ። Ver Capítulo |