Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 41:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 በመ​ቅ​ደ​ሱም ፊት ርዝ​መ​ቱን አርባ ክንድ፥ ወር​ዱ​ንም ሃያ ክንድ አድ​ርጎ ለካና፥ “ይህ ቅድ​ስተ ቅዱ​ሳን ነው” አለኝ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እርሱም የውስጠኛውን መቅደስ ርዝመት ለካ፤ ሃያ ክንድ ነበር፤ ወርዱም የውጪውን ግድግዳ ጨምሮ ሃያ ክንድ ነበር፤ እርሱም፣ “ይህ ቅድስተ ቅዱሳን ነው” አለኝ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 በመቅደሱ ፊት ያለውን ርዝመቱን ሀያ ክንድ ወርዱንም ሀያ ክንድ አድርጎ ለካና፦ “ይህ ቅድስተ ቅዱሳን ነው” አለኝ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ከመካከለኛው ክፍል ባሻገር ያለውን ውስጠኛ ክፍል ከማእዘን እስከ ማእዘን ሲለካ ርዝመቱ ኻያ ክንድ ወርዱም ኻያ ክንድ ሆነ፤ ከዚያም በኋላ “ይህ ቅድስተ ቅዱሳን ነው” አለኝ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 በመቅደሱም ፊት ርዘመቱን ሀያ ክንድ ወርዱንም ሀያ ክንድ አድርጎ ለካና፦ ይህ ቅድስተ ቅዱሳን ነው አለኝ።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 41:4
11 Referencias Cruzadas  

ከቤተ መቅ​ደሱ አያ​ይዞ ከመ​ሠ​ረቱ ጀምሮ እስከ ጣራው ድረስ ሃያ​ውን ክንድ በዝ​ግባ ጠርብ ሠራ፤ ከመ​ቅ​ደ​ሱም ከፍሎ ቅድ​ስተ ቅዱ​ሳ​ኑን አደ​ረገ።


የቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳ​ኑም ርዝ​መት ሃያ ክንድ፥ ስፋ​ቱም ሃያ ክንድ፥ ቁመ​ቱም ሃያ ክንድ ነበረ፤ በጥ​ሩም ወርቅ ለበ​ጠው።


በቤ​ቱም ግንብ ዙሪያ፥ በመ​ቅ​ደ​ሱና በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳኑ ግንብ ዙሪያ ደርብ ሠራ፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ጓዳ​ዎች አደ​ረገ።


ከጥሩ ወር​ቅም የተ​ሠ​ሩ​ትን ጽዋ​ዎ​ችና ጕጠ​ቶች፥ ድስ​ቶ​ቹ​ንና ጭል​ፋ​ዎ​ቹ​ንም፥ ማን​ደ​ጃ​ዎ​ቹ​ንም፥ ጽን​ሐ​ሖ​ችን፥ ለው​ስ​ጠ​ኛ​ውም ቤት ለቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳን ደጆች፥ ለቤተ መቅ​ደ​ሱም ደጆች የሚ​ሆ​ኑ​ትን የወ​ርቅ ማጠ​ፊ​ያ​ዎች አሠራ።


ካህ​ና​ቱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን ታቦት በቤቱ በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳን ውስጥ ከኪ​ሩ​ቤል ክንፍ በታች ወደ ነበ​ረው ወደ ስፍ​ራዋ አገቧት።


ቅድ​ስተ ቅዱ​ሳ​ኑ​ንም ሠራ፤ ርዝ​መ​ቱም እንደ ቤቱ ወርድ ሃያ ክንድ፥ ወር​ዱም ሃያ ክንድ ነበረ፤ ስድ​ስት መቶ መክ​ሊት በሚ​ያ​ህል በጥሩ ወር​ቅም ኪሩ​ቤ​ልን ለበ​ጣ​ቸው።


ካህ​ና​ቱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳን ታቦት ወደ ቤትዋ አም​ጥ​ተው በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳን ውስጥ ከኪ​ሩ​ቤል ክንፍ በታች በነ​በ​ረው መቅ​ደስ አኖ​ሯት።


ለመ​ቅ​ደ​ሱና ለተ​ቀ​ደ​ሰው ስፍራ ሁለት መዝ​ጊ​ያ​ዎች ነበ​ሩ​አ​ቸው።


ከተማይቱም አራት ማዕዘን ነበራት፤ ርዝመትዋም እንደ ስፋትዋ ልክ ነበረ። ከተማይቱንም በዘንግ ለካት፤ ሁለት ሺህ አራት መቶ ኪሎ ሜትር ሆነች፤ ርዝመትዋና ስፋትዋ ከፍታዋም ትክክል ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos