Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 41:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ወደ ውስ​ጥም ገባ፤ የመ​ግ​ቢ​ያ​ው​ንም የግ​ንብ አዕ​ማድ ወርድ ሁለት ክንድ አድ​ርጎ ለካ፤ የመ​ግ​ቢ​ያ​ውም ወርድ ስድ​ስት ክንድ ነበረ፤ የመ​ግ​ቢ​ያ​ውም ግንብ ወርድ በዚህ ወገን ሰባት ክንድ፥ በዚ​ያም ወገን ሰባት ክንድ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ከዚያም ወደ ውስጥ ገባ፤ የመግቢያውን ዐምዶች ለካ፤ የእያንዳንዱም ወርድ ሁለት ክንድ ነበር። የመግቢያውም ወርድ ስድስት ክንድ ሲሆን፣ ግራና ቀኝ ወጣ ወጣ ያሉት ግንቦች ወርድ ደግሞ ሰባት ክንድ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ወደ ውስጥም ገብቶ የመግቢያውን ዓምድ ወርድ ሁለት ክንድ፥ የመግቢያውም ወርድ ስድስት ክንድ ነበረ፥ የመግቢያውም ግንብ ወርድ ሰባት ክንድ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ከዚያም አልፎ ወደ ውስጠኛው ክፍል ገባ፤ ወደ እርሱ የሚያስገባውንም መተላለፊያ ሲለካው ርዝመቱ ሁለት ክንድ ወርዱ ስድስት ክንድ ሆነ፤ በግራና ቀኝ የሚገኙትም ግንቦች የእያንዳንዱ ውፍረት ሰባት ክንድ ሆነ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ወደ ውስጥም ገባ፥ የመግቢያውንም የግንብ አዕማድ ወርድ ሁለት ክንድ አድርጎ ለካ፥ የመግቢያውም ወርድ ስድስት ክንድ ነበረ፥ የመግቢያውም ግንብ ወርድ በዚህ ወገን ሰባት ክንድ በዚያም ወገን ሰባት ክንድ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 41:3
3 Referencias Cruzadas  

በዕቃ ቤቶ​ቹም በበሩ ውስጥ በዙ​ሪ​ያው በነ​በ​ሩ​ትም በግ​ንቡ አዕ​ማድ የዐ​ይነ ርግብ መስ​ኮ​ቶች ነበ​ሩ​ባ​ቸው፤ ደግ​ሞም በደጀ ሰላሙ ውስጥ በዙ​ሪ​ያው መስ​ኮ​ቶች ነበሩ፤ በግ​ን​ቡም አዕ​ማድ ሁሉ ላይ የዘ​ን​ባባ ዛፍ ተቀ​ር​ጾ​ባ​ቸው ነበር።


ወደ ቤቱም ደጀ ሰላም አመ​ጣኝ፤ የደጀ ሰላ​ሙ​ንም የግ​ንብ አዕ​ማድ ወርድ በዚህ ወገን አም​ስት ክንድ፤ በዚ​ያም ወገን አም​ስት ክንድ አድ​ርጎ ለካ፤ የበ​ሩም ወርድ ዐሥራ አራት ክንድ ነበረ፤ በበ​ሩም በዚህ ወገ​ንና በዚያ ወገን የነ​በ​ሩት ግን​ቦች ሦስት ሦስት ክንድ ነበሩ።


ወደ መቅ​ደ​ሱም አገ​ባኝ፤ የግ​ን​ቡ​ንም አዕ​ማድ ወርድ በዚህ ወገን ስድ​ስት ክንድ፥ በዚ​ያም ወገን ስድ​ስት ክንድ አድ​ርጎ ለካ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos