Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 3:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 እን​ዲ​ህም አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! ተነ​ሥ​ተህ ወደ እስ​ራ​ኤል ቤት ሂድና ግባ፥ ቃሌ​ንም ንገ​ራ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “የሰው ልጅ ሆይ፤ ተነሥተህ ወደ እስራኤል ቤት ሂድ፤ ቃሌንም ንገራቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 እንዲህም አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ ተነሥተህ ወደ እስራኤል ቤት ሂድ፥ ቃሌንም ንገራቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! ወደ እስራኤል ሕዝብ ሄደህ እኔ የምነግርህን ቃል ንገራቸው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 እንዲህም አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ ተነሥተህ ወደ እስራኤል ቤት ሂድ፥ ቃሌንም ተናገራቸው።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 3:4
12 Referencias Cruzadas  

ያየ​ሁ​ትም ራእይ ከእኔ ወጣ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያሳ​የ​ኝን ነገር ሁሉ ለም​ር​ኮ​ኞች ተና​ገ​ርሁ።


ስለ​ዚህ የሰው ልጅ ሆይ! ትን​ቢት ተና​ገ​ር​ባ​ቸው፤ ትን​ቢት ተና​ገር።”


እር​ሱም እን​ዲህ አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! እኔን ወደ አስ​መ​ረ​ሩኝ ወደ እስ​ራ​ኤል ቤት እል​ክ​ሃ​ለሁ። እነ​ር​ሱና አባ​ቶ​ቻ​ቸው እስከ ዛሬ ድረስ ዐመ​ፁ​ብኝ።


እነ​ርሱ ፊታ​ቸው የከፋ፥ ልባ​ቸው የደ​ነ​ደነ ልጆች ናቸው። እኔ ወደ እነ​ርሱ እል​ክ​ሃ​ለሁ፤ አን​ተም፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል በላ​ቸው።


እነ​ርሱ ዐመ​ፀኛ ቤት ስለ​ሆኑ ቢሰሙ ወይም ቢደ​ነ​ግጡ ቃሌን ትነ​ግ​ራ​ቸ​ዋ​ለህ።


“ስለ​ዚህ የሰው ልጅ ሆይ! ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ተና​ገር፤ እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በዚ​ህም ደግሞ አባ​ቶ​ቻ​ችሁ በአ​ደ​ረ​ጉት ዐመፅ አስ​ቈ​ጡኝ።


ተነ​ሥ​ተ​ህም ወደ ተማ​ረኩ ወደ ወገ​ንህ ልጆች ሂድ፤ እነ​ር​ሱም ቢሰሙ ወይም ቢፈሩ፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል ብለህ ንገ​ራ​ቸው” አለኝ።


እር​ሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! አፍህ ይብላ፤ በም​ሰ​ጥ​ህም በዚህ መጽ​ሐፍ ሆድ​ህን ሙላ” አለኝ። እኔም በላ​ሁት፤ በአ​ፌም ውስጥ እንደ ማር ጣፈጠ።


ወደ እስ​ራ​ኤል ቤት እንጂ ንግ​ግ​ራ​ቸው ልዩ ወደ ሆነ፥ ቋን​ቋ​ቸ​ውም ወደ​ማ​ይ​ታ​ወቅ ሕዝብ አል​ተ​ላ​ክ​ህ​ምና፤


እርሱም መልሶ “ከእስራኤል ቤት ለጠፉት በጎች በቀር አልተላክሁም፤” አለ።


ነገር ግን መን​ፈስ ቅዱስ በእ​ና​ንተ ላይ በወ​ረደ ጊዜ ኀይ​ልን ትቀ​በ​ላ​ላ​ችሁ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና በይ​ሁዳ ሁሉ፥ በሰ​ማ​ር​ያና እስከ ምድር ዳርቻ ድረ​ስም ምስ​ክ​ሮች ትሆ​ኑ​ኛ​ላ​ችሁ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos