Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 2:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 “እነ​ርሱ ዐመ​ፀኛ ቤት ናቸ​ውና ቢሰሙ ወይም ቢፈሩ አንተ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ነቢይ እንደ ሆንህ ያው​ቃሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 እነርሱ ዐመፀኛ ቤት ስለ ሆኑ፤ ቢሰሙም ባይሰሙም በመካከላቸው ነቢይ እንደ ነበር ያውቃሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 እነርሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸውና ቢሰሙ ወይም ባይሰሙ በመካከላቸው ነቢይ እንደ ነበረ ያውቃሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እነዚያ ዐመፀኞች ቢሰሙህም ባይሰሙህም ነቢይ በመካከላቸው መኖሩን ያውቃሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 እነርሱም ዓመፀኛ ቤት ናቸውና ቢሰሙ ወይም ባይሰሙ ነቢይ በመካከላቸው እንዳለ ያውቃሉ።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 2:5
20 Referencias Cruzadas  

ኤል​ሳ​ዕም የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ልብ​ሱን እንደ ቀደደ በሰማ ጊዜ፥ “ልብ​ስ​ህን ለምን ቀደ​ድህ? ንዕ​ማን ወደ እኔ ይምጣ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ ነቢይ እን​ዳለ ያው​ቃል” ብሎ ወደ ንጉሡ ላከ።


ንጉ​ሡም ክር​ታ​ሱን ያመጣ ዘንድ ይሁ​ዳን ላከ፤ እር​ሱም ከጸ​ሓ​ፊው ከኤ​ሊ​ሳማ ክፍል ወሰ​ደው፤ ይሁ​ዳም በን​ጉ​ሡና በን​ጉሡ አጠ​ገብ በቆ​ሙት አለ​ቆች ሁሉ ጆሮ አነ​በ​በው።


እና​ንተ የይ​ሁዳ ቅሬታ ሆይ! እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ ወደ ግብፅ አት​ግቡ ብሎ ተና​ግ​ሮ​ባ​ች​ኋ​ልና ዛሬ እን​ዳ​ስ​ጠ​ነ​ቀ​ቅ​ኋ​ችሁ በእ​ር​ግጥ ዕወቁ።


“የሰው ልጅ ሆይ! ዐመ​ፀኛ ቤት የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት፦ የም​ታ​ደ​ር​ገው ምን​ድር ነው? አላ​ሉ​ህ​ምን?


“የሰው ልጅ ሆይ፥ ለአ​ስ​ቈ​ጡኝ ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ይህ ትር​ጓሜ ምን እንደ ሆነ አታ​ው​ቁ​ምን? በላ​ቸው። እን​ዲ​ህም ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ እነሆ የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መጣ፤ ንጉ​ሥ​ዋ​ንና መኳ​ን​ን​ቶ​ች​ዋ​ንም ማረከ፤ ወደ ሀገ​ሩም ወደ ባቢ​ሎን ወሰ​ዳ​ቸው።


እነ​ርሱ ዐመ​ፀኛ ቤት ስለ​ሆኑ ቢሰሙ ወይም ቢደ​ነ​ግጡ ቃሌን ትነ​ግ​ራ​ቸ​ዋ​ለህ።


ለዐ​መ​ፀ​ኛ​ውም ቤት ምሳ​ሌን ተና​ገር እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ጣድ፥ ድስ​ቲ​ቱን ጣድ፥ ውኃም ጨም​ር​ባት።


ነገር ግን አንተ ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውን ብት​ገ​ሥ​ጸው እር​ሱም ከኀ​ጢ​አ​ቱና ከክፉ መን​ገዱ ባይ​መ​ለስ፥ በኀ​ጢ​አቱ ይሞ​ታል፤ አንተ ግን ነፍ​ስ​ህን ታድ​ና​ለህ።


እኔም ምላ​ስ​ህን ከት​ና​ጋህ ጋር አጣ​ብ​ቃ​ታ​ለሁ፤ አን​ተም ዲዳ ትሆ​ና​ለህ፤ እነ​ር​ሱም ዐመ​ፀኛ ቤት ናቸ​ውና የሚ​ዘ​ልፍ ሰው አት​ሆ​ን​ባ​ቸ​ውም።


ነገር ግን በተ​ና​ገ​ር​ሁህ ጊዜ አፍ​ህን እከ​ፍ​ታ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ዐመ​ፀኛ ቤት ናቸ​ውና አንተ፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የሚ​ሰማ ይስማ፤ እንቢ የሚ​ልም እንቢ ይበል” ትላ​ቸ​ዋ​ለህ።


እነ​ር​ሱም እን​ዲህ ይላሉ፦ እነሆ ይህ ይመ​ጣል፤ በመ​ጣም ጊዜ እነ​ርሱ ነቢይ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው እንደ ነበረ ያው​ቃሉ።”


ነገር ግን ከመ​ን​ገዱ ይመ​ለስ ዘንድ ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውን ብታ​ስ​ጠ​ነ​ቅ​ቀው፥ እር​ሱም ከመ​ን​ገዱ ባይ​መ​ለስ፥ በኀ​ጢ​አቱ ይሞ​ታል፤ አንተ ግን ነፍ​ስ​ህን ታድ​ና​ለህ።


ለዐ​መ​ፀ​ኛው ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት እን​ዲህ በል፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! ርኵ​ሰ​ታ​ችሁ ሁሉ ይብ​ቃ​ችሁ።


ባል​መ​ጣ​ሁና ባል​ነ​ገ​ር​ኋ​ቸ​ውስ ኖሮ ኀጢ​አት ባል​ሆ​ነ​ባ​ቸ​ውም ነበር፤ አሁን ግን ለኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው ምክ​ን​ያት የላ​ቸ​ውም።


ጳው​ሎ​ስና በር​ና​ባ​ስም ደፍ​ረው እን​ዲህ ብለው ተና​ገ​ሩ​አ​ቸው፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ለእ​ና​ንተ አስ​ቀ​ድሞ ልን​ነ​ግ​ራ​ችሁ ይገ​ባል፤ እንቢ ብት​ሉና ራሳ​ች​ሁን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት የተ​ዘ​ጋጀ ባታ​ደ​ርጉ ግን እነሆ፥ ወደ አሕ​ዛብ እን​መ​ለ​ሳ​ለን።


የማ​ያ​ምኑ ቢኖ​ሩስ የእ​ነ​ርሱ አለ​ማ​መን ሌላ​ውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ያ​ምን ይከ​ለ​ክ​ላ​ልን? አይ​ከ​ለ​ክ​ልም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos