Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 33:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ሙሴም ወደ ድን​ኳኑ በገባ ጊዜ ዐምደ ደመና ይወ​ርድ ነበር፤ በድ​ን​ኳ​ኑም ደጃፍ ይቆም ነበር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን ይና​ገ​ረው ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ሙሴ ወደ ድንኳኑ ገብቶ እግዚአብሔር ከሙሴ ጋራ እየተነጋገረ ሳለ የደመናው ዐምድ ወርዶ በመግቢያው ላይ ይቆም ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ሙሴ ወደ ድንኳኑ በሚገባበት ጊዜ የደመና ዓምድ ይወርድ ነበር፥ በድንኳኑ ደጃፍ ይቆም ነበር፤ ጌታም ሙሴን ያናግረው ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ሙሴም ወደዚያ ከገባ በኋላ የደመናው ዐምድ ወርዶ በድንኳኑ ደጃፍ ይቆማል፤ እግዚአብሔርም በደመናው ውስጥ ሆኖ ሙሴን ያነጋግረው ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ሙሴም ወደ ድንኳኑ በገባ ጊዜ የደመና ዓምድ ይወርድ ነበር፥ በድንኳኑም ደጃፍ ይቆም ነበር፤ እግዚአብሔርም ሙሴን ይናገረው ነበር።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 33:9
17 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ንግ​ግ​ሩን ከእ​ርሱ ጋር በፈ​ጸመ ጊዜ ከአ​ብ​ር​ሃም ተለ​ይቶ ወጣ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከአ​ብ​ር​ሃም ጋር ንግ​ግ​ሩን በጨ​ረሰ ጊዜ ሄደ፤ አብ​ር​ሃ​ምም ወደ ስፍ​ራው ተመ​ለሰ።


በዚ​ያም እገ​ለ​ጥ​ል​ሃ​ለሁ፤ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የማ​ዝ​ዝ​ህን ሁሉ፥ በም​ስ​ክሩ ታቦት ላይ ባለው በሁ​ለት ኪሩ​ቤል መካ​ከል፥ በስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ውም ላይ ሆኜ እነ​ጋ​ገ​ር​ሃ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ርሱ ጋር በሲና ተራራ የተ​ና​ገ​ረ​ውን በፈ​ጸመ ጊዜ ሁለ​ቱን የም​ስ​ክር ጽላት፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጣት የተ​ጻ​ፈ​ባ​ቸ​ውን የድ​ን​ጋይ ጽላት ለሙሴ ሰጠው።


ሕዝ​ቡም ሁሉ ዐምደ ደመ​ናው በድ​ን​ኳኑ ደጃፍ ሲቆም ያየው ነበር፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ተነ​ሥቶ እያ​ን​ዳ​ንዱ በድ​ን​ኳኑ ደጃፍ ይሰ​ግድ ነበር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ ሰው ከባ​ል​ን​ጀ​ራው ጋር እን​ደ​ሚ​ነ​ጋ​ገር ፊት ለፊት ከሙሴ ጋር ይነ​ጋ​ገር ነበር። ሙሴም ወደ ሰፈሩ ይመ​ለስ ነበር፤ ነገር ግን አገ​ል​ጋዩ ብላ​ቴና የነዌ ልጅ ኢያሱ ከድ​ን​ኳኑ አይ​ወ​ጣም ነበር።


ሙሴም ከሰ​ፈር ውጭ ወደ​አ​ለው ድን​ኳን በሄደ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ፥ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም በድ​ን​ኳኑ ደጃፍ እየ​ጠ​በቀ ይቆም ነበር፤ ሙሴም ወደ ድን​ኳኑ እስ​ኪ​ገባ ድረስ ይመ​ለ​ከ​ቱት ነበር።


ከአ​ን​ተም ጋር ማንም ሰው አይ​ውጣ፤ በተ​ራ​ራ​ውም ሁሉ ማንም አይ​ታይ፤ መን​ጎ​ችና ከብ​ቶ​ችም በዚያ ተራራ አጠ​ገብ አይ​ሰ​ማሩ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በደ​መ​ናው ውስጥ ወረደ፤ በዚ​ያም ከእ​ርሱ ጋር ቆመ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስም ጠራ።


“አቤቱ በፊ​ት​ህስ ሞገ​ስን አግ​ኝቼ እንደ ሆነ፥ ይህ ሕዝብ አን​ገተ ደን​ዳና ነውና ጌታዬ ከእኛ ጋር ይሂድ፤ ጠማ​ማ​ነ​ታ​ች​ንን፥ ኀጢ​አ​ታ​ች​ን​ንና በደ​ላ​ች​ንን ይቅር በለን፤ ለአ​ን​ተም እን​ሆ​ና​ለን” አለ።


በዚ​ያም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በእኔ ላይ ነበ​ረች፤ እር​ሱም፥ “ተነ​ሥ​ተህ ወደ ሜዳ ሂድ፤ በዚ​ያም እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ” አለኝ።


እኔም እወ​ር​ዳ​ለሁ፤ በዚ​ያም አነ​ጋ​ግ​ር​ሃ​ለሁ፤ በአ​ንተ ካለ​ውም መን​ፈስ ወስጄ በእ​ነ​ርሱ ላይ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ፤ አን​ተም ብቻ እን​ዳ​ት​ሸ​ከም የሕ​ዝ​ቡን ሸክም ከአ​ንተ ጋር ይሸ​ከ​ማሉ።


ሙሴም ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን እር​ሱን ለመ​ነ​ጋ​ገር በገባ ጊዜ በቃል ኪዳኑ ታቦት ላይ ካለው ከስ​ር​የት መክ​ደ​ኛው በላይ ከኪ​ሩ​ቤ​ልም መካ​ከል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ድምፅ ይሰማ ነበር፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ይና​ገር ነበር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “የም​ት​ሞ​ት​በት ቀን እነሆ ቀረበ፤ ኢያ​ሱን ጠር​ተህ እር​ሱን አዝ​ዘው ዘንድ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ከእ​ርሱ ጋር ቁም” አለው። ሙሴና ኢያ​ሱም ሄደው በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ቆሙ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ በደ​መና ዐምድ ወረደ፤ የደ​መ​ና​ውም ዐምድ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ላይ ቆመ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos