Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 6:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 “ሕዝ​ብ​ህም ጠላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ለመ​ው​ጋት አንተ በም​ት​ል​ካ​ቸው መን​ገድ ቢወጡ፥ አን​ተም ወደ መረ​ጥ​ሃት ወደ​ዚ​ህች ከተማ፥ እኔም ለስ​ምህ ወደ ሠራ​ሁት ቤት ለአ​ንተ ቢጸ​ልዩ፥

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 “ሕዝብህ ጠላቶቻቸውን ለመውጋት አንተ ወደምትልካቸው ቦታ ሁሉ በሚወጡበት ጊዜ፣ አንተ ወደ መረጥሃት ወደዚህች ከተማ፣ እኔም ለስምህ ወደ ሠራሁት ቤተ መቅደስ ወደ አንተ ቢጸልዩ፣

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 “ሕዝብህም ጠላቶቻቸውን ለመውጋት አንተ በምትልካቸው መንገድ ቢወጡ፥ አንተም ወደ መረጥሃት ወደዚህች ከተማ እኔም ለስምህ ወደ ሠራሁት ቤት ለአንተ ቢጸልዩ፥

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 “ጠላቶቻቸውን ለመውጋት እንዲዘምቱ ሕዝብህን በምታዝበት ጊዜ በየትኛውም ስፍራ ሆነው ወደዚህች ወደ መረጥኻት ከተማና እኔ ለአንተ ወደ ሠራሁት ወደዚህ ቤተ መቅደስ ፊታቸውን መልሰው በሚጸልዩበት ጊዜ፥

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 “ሕዝብህም ጠላቶቻቸውን ለመውጋት አንተ በምትልካቸው መንገድ ቢወጡ፥ አንተም ወደ መረጥሃት ወደዚህች ከተማ እኔም ለስምህ ወደ ሠራሁት ቤት ለአንተ ቢጸልዩ፥

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 6:34
19 Referencias Cruzadas  

እኔም ለዘ​ለ​ዓ​ለም የም​ት​ኖ​ር​በ​ትን ማደ​ሪያ ቤት በእ​ው​ነት ሠራ​ሁ​ልህ።”


የሰ​ረ​ገ​ሎ​ችም አለ​ቆች ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን ባዩ ጊዜ፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ነው” አሉ፤ ሊጋ​ጠ​ሙ​ትም ከበ​ቡት፤ ኢዮ​ሣ​ፍጥ ግን ጮኸ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አዳ​ነው፤ አም​ላ​ኩም ከእ​ርሱ መለ​ሳ​ቸው።


ይሁ​ዳም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይፈ​ልግ ዘንድ ተሰ​በ​ሰበ፤ ከይ​ሁዳ ከተ​ሞ​ችም ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይፈ​ልጉ ዘንድ መጡ።


አንተ በማ​ደ​ሪ​ያህ በሰ​ማይ ስማ፤ የም​ድ​ርም አሕ​ዛብ ሁሉ ስም​ህን ያውቁ ዘንድ፥ እንደ ሕዝ​ብ​ህም እንደ እስ​ራ​ኤል ይፈ​ሩህ ዘንድ፥ በዚ​ህም በሠ​ራ​ሁት ቤት ስምህ እንደ ተጠራ ያውቁ ዘንድ፥ እን​ግ​ዳው የሚ​ለ​ም​ን​ህን ሁሉ አድ​ርግ።


ጸሎ​ታ​ቸ​ው​ንና ልመ​ና​ቸ​ውን በሰ​ማይ ስማ፤ ፍር​ድ​ንም ፍረ​ድ​ላ​ቸው።


ነገር ግን ስሜ በዚያ እን​ዲ​ጠ​ራ​ባት ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን መር​ጫ​ለሁ። በሕ​ዝ​ቤም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ እን​ዲ​ሆን ዳዊ​ትን መር​ጫ​ለሁ ብሎ​አል።


የአ​ሕ​ዛብ ነገ​ሥ​ታት ምን ይመ​ል​ሳሉ? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽዮ​ንን መሠ​ረ​ታት፤ ትሑ​ታን የሆ​ኑ​ት​ንም ሕዝብ አዳ​ና​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ ሄደህ ኀጢ​ኣ​ተ​ኞ​ቹን አማ​ሌ​ቃ​ው​ያ​ንን ፈጽ​መህ አጥ​ፋ​ቸው፤ እስ​ኪ​ጠ​ፉም ድረስ ውጋ​ቸው ብሎ በመ​ን​ገድ ላከህ።


አሁ​ንም ሄደህ አማ​ሌ​ቅ​ንና ኢያ​ሬ​ምን ምታ፤ ያላ​ቸ​ው​ንም ሁሉ ፈጽ​መህ አጥፋ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የም​ታ​ድ​ነው የለም። አጥ​ፋ​ቸው፤ መከ​ራም አጽ​ና​ባ​ቸው፤ የእ​ነ​ርሱ የሆ​ነ​ውን ሁሉ አጥፋ፤ ለያ​ቸ​ውም፤ አት​ማ​ራ​ቸ​ውም፤ ወን​ዱ​ንና ሴቱን፥ ብላ​ቴ​ና​ው​ንና ሕፃ​ኑን፥ በሬ​ው​ንና በጉን፥ ግመ​ሉ​ንና አህ​ያ​ውን ግደል።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos