Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 31:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ለአ​ገ​ል​ግ​ሎት እን​ዲ​ጸኑ ለካ​ህ​ና​ቱና ለሌ​ዋ​ው​ያን ድር​ሻ​ቸ​ውን ይሰጡ ዘንድ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሕዝብ አዘዘ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ካህናቱና ሌዋውያኑም ሙሉ ጊዜያቸውን ለእግዚአብሔር ሕግ አገልግሎት ማዋል ይችሉ ዘንድ፣ በኢየሩሳሌም የሚኖረው ሕዝብ ተገቢውን ድርሻ እንዲሰጣቸው አዘዘ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 የጌታንም ሕግ በጽኑ እንዲያገለግሉ ለካህናቱና ለሌዋውያኑ የሚገባቸውን ድርሻ እንዲሰጡአቸው በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ሕዝብ አዘዘ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 በተጨማሪም ካህናቱና ሌዋውያኑ ጊዜአቸውን በሙሉ የእግዚአብሔር ሕግ ለሚጠይቀው አገልግሎት ማዋል ይችሉ ዘንድ ለእነርሱ መሰጠት የሚገባውን ሁሉ የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች እንዲያመጡ ንጉሡ አዘዘ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 በእግዚአብሔርም ቤት ለአገልግሎት እንዲጸኑ ለካህናቱና ለሌዋውያን ክፍላቸውን ይሰጡ ዘንድ በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ሕዝብ አዘዘ።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 31:4
12 Referencias Cruzadas  

ከሦ​ስ​ትም ዓመት ወደ ላይ ላሉ በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው ለሥ​ራ​ቸ​ውና ለአ​ገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸው ዕለት ዕለት ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ለሚ​ገቡ ወን​ዶች ሁሉ፥


የበ​ኵ​ራቱ ሁሉ መጀ​መ​ሪያ ከየ​ዓ​ይ​ነቱ፥ ከቍ​ር​ባ​ና​ች​ሁም ሁሉ የማ​ን​ሣት ቍር​ባን ሁሉ ለካ​ህ​ናት ይሆ​ናል፤ በቤ​ታ​ች​ሁም ውስጥ በረ​ከት ያድር ዘንድ የአ​ዝ​መ​ራ​ች​ሁን ቀዳ​ም​ያት ለካ​ህ​ናቱ ትሰ​ጣ​ላ​ችሁ።


ካህኑ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር መልእክተኛ ነውና ከንፈሮቹ እውቀትን ይጠብቁ ዘንድ ይገባቸዋል፥ ሰዎችም ሕግን ከአፉ ይፈልጉ ዘንድ ይገባቸዋል።


ይህ​ንም ነገር ንኡሰ ክር​ስ​ቲ​ያን ይስ​ማው፤ መል​ካ​ሙ​ንም ነገር ሁሉ ከሚ​ያ​ስ​ተ​ም​ረው ይማር።


ከአ​ባ​ቶቹ ከብት ዋጋ ሌላ እንደ ባል​ን​ጀ​ሮቹ ከመ​ብል ድር​ሻ​ውን ይወ​ስ​ዳል።


ከሌዊ ልጆ​ችም፥ ክህ​ነ​ትን የሚ​ቀ​በ​ሉት ከሕ​ዝቡ ማለት ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው፥ እነ​ርሱ ምንም ከአ​ብ​ር​ሃም ወገብ ቢወጡ ከእ​ነ​ርሱ ዐሥ​ራ​ትን በሕግ እን​ዲ​ያ​ስ​ወጡ ትእ​ዛዝ አላ​ቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos