Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 31:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ሕዝ​ቅ​ያ​ስም በይ​ሁዳ ሁሉ እን​ዲህ አደ​ረገ፤ በአ​ም​ላ​ኩም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት መል​ካ​ም​ንና ቅን ነገ​ርን እው​ነ​ት​ንም አደ​ረገ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ሕዝቅያስ በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት መልካም፣ ቅንና ታማኝ ሆኖ በመገኘት በመላው ይሁዳ የፈጸመው ተግባር ይህ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ሕዝቅያስም በይሁዳ ሁሉ እንዲህ አደረገ፤ በአምላኩም በጌታ ፊት መልካምንና ቅንን ነገር እውነትንም አደረገ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ንጉሥ ሕዝቅያስ በመላው የይሁዳ ግዛት መልካም የሆነውንና ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኘውን ነገር ሁሉ አደረገ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ሕዝቅያስም በይሁዳ ሁሉ እንዲህ አደረገ፤ በአምላኩም በእግዚአብሔር ፊት መልካምንና ቅንን ነገር እውነትንም አደረገ።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 31:20
11 Referencias Cruzadas  

ከኬ​ጥ​ያ​ዊው ከኦ​ርዮ ነገር በቀር ዳዊት በዘ​መኑ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቅን ነገ​ርን አድ​ርጎ ነበ​ርና፥ ካዘ​ዘ​ውም ነገር ሁሉ ፈቀቅ አላ​ለም ነበ​ርና።


እር​ሱም አባቱ ዳዊት እን​ዳ​ደ​ረ​ገው ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቅን ነገ​ርን አደ​ረገ።


“አቤቱ፥ በፊ​ትህ በእ​ው​ነ​ትና በፍ​ጹም ልብ እንደ ሄድሁ፥ መል​ካም ነገ​ርም እን​ዳ​ደ​ረ​ግሁ አስብ።” ሕዝ​ቅ​ያ​ስም እጅግ አለ​ቀሰ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ቅን ነገ​ርን አደ​ረገ፤ በአ​ባ​ቱም በዳ​ዊት መን​ገድ ሁሉ ሄደ፤ ቀኝም ግራም አላ​ለም።


አብ​ያም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፤ በዳ​ዊ​ትም ከተማ ቀበ​ሩት፤ ልጁም አሳ በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ። በእ​ር​ሱም ዘመን ምድ​ሪቱ ዐሥር ዓመት ያህል ዐረ​ፈች።


ዙፋን በም​ሕ​ረት ይጸ​ናል፥ በዚ​ያም ላይ በዳ​ዊት ቤት ፍር​ድን የሚሻ ጽድ​ቅ​ንም የሚ​ያ​ፋ​ጥን ፈራጅ በእ​ው​ነት ይቀ​መ​ጣል፤ ይፈ​ር​ዳ​ልም።


አምስት መክሊትም የተቀበለው ሄዶ ነገደበት፤ ሌላም አምስት አተረፈ፤


ናት​ና​ኤ​ልም፥ “በውኑ ከና​ዝ​ሬት ደግ ሰው ሊወጣ ይቻ​ላ​ልን?” አለው፤ ፊል​ጶ​ስም፥ “መጥ​ተህ እይ” አለው።


እን​ዲሁ እኔም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና በሰው ፊት ሁል​ጊዜ የማ​ታ​ወ​ላ​ውል ሕሊና ትኖ​ረኝ ዘንድ እጋ​ደ​ላ​ለሁ።


በእናንተ በምታምኑ ዘንድ እንዴት ባለ ቅድስናና ጽድቅ ነቀፋም በሌለበት ኑሮ እንደ ሄድን፥ እናንተና እግዚአብሔር ምስክሮች ናችሁ፤


ወዳጅ ሆይ! ምንም እንግዶች ቢሆኑ፥ ለወንድሞች በምታደርገው ሁሉ የታመነ ሥራ ትሠራለህ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos